የምግብ መብት የመንግሥት ችሮታ ተደርጎ ሊወሰድ ወይም ለፖለቲካ ፍጆታ ሊውል አይገባም ሲል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ገለ

- Advertisement -
Sidebar AD

የምግብ መብት የመንግሥት ችሮታ ተደርጎ ሊወሰድ ወይም ለፖለቲካ ፍጆታ ሊውል አይገባም ሲል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ገለጸ

አሐዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ ባዘጋጀው የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ የፓርቲያቸውን የፖሊሲ አማራጭ ያቀረቡት የአብን ተወካይ አቶ ኤርሚያስ ተገኔ፣ የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ለማረጋገጥ መሠረታዊ የፖሊሲ ለውጦች እንደሚያስፈልጉ ገልጸዋል።

በመድረኩ ዜጎች ምግብ የማግኘት መብታቸውን መነሻ በማድረግ መንግሥትን በቀጥታ ፍርድ ቤት የመክሰስ መብት ሊኖራቸው ይገባል ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ “እንዲህ ዓይነት ውሳኔዎች ለምርጫ ክርክር ፍጆታ ብቻ የሚውሉ የማይጨበጡ ሕልሞች መሆን የለባቸውም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አስገዳጅ ሕጎች ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ እና የኢኮኖሚ አቅም ላይ የተመሠረቱ መሆን እንደሚገባቸው ተወካዩ አብራርተዋል።

ፓርቲያቸው በአሁኑ ወቅት ያሉትን የምገባ ማዕከላት ከመዋጮ አሠራር በጸዳ መልኩ በቀጥታ ከመንግሥት በጀት እንዲደጎሙ የማድረግ አቅጣጫ እንዳለው አቶ ኤርሚያስ ጠቁመዋል።

አክለውም፤ የምገባ ሥርዓቱ ጊዜያዊ ችግር መፍቻ እንጂ ዘላቂ መሆን እንደሌለበት በመጥቀስ፣ ዜጎች ለችግር እንዲጋለጡ የሚያደርጉትን እንደ ሕገ-መንግሥት፣ መልካም አስተዳደር እና አግላይ ፖሊሲዎች ያሉ ገፊ ምክንያቶችን በዘላቂነት መቅረፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የዜጎችን የምግብ ዋስትና ደረጃ በደረጃ ለማቃለል የማዳበሪያ እና የዘር እጥረት ችግርን መፍታት እንዲሁም በየክልሉ የምግብ ክምችት ማዕከላትን መገንባት እንደሚያስፈልግ በመድረኩ ተገልአል።

ምግብ ሲባል የአዕምሮ እና መንፈሳዊ ምግብም ጭምር መሆኑን የጠቀሱት አቶ ኤርሚያስ፣ ብቁ ዜጋ ለማፍራት ሁለንተናዊ የምገባ ሥርዓት ለመገንባት ፓርቲያቸው እንደሚታገል አስታውቀዋል።

አሐዱ ሬዲዮ


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1