የቡኖ ማላ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በዲላ ከተማ በደመቀ ሁኔታ መካሄድ ጀመረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቡኖ ማላ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ በሚገኘው የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በይፋ ተከፍቷል።

ይህ ታላቅ መድረክ የጌዴኦን የቡናና የሥጋ ምርት ሀብት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የዲላን የኢንቨስትመንት ሳቢነት ለማሳደግ እንዲሁም በየአካባቢው የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለዓለም ማህበረሰብ በሰፊው ለማስተዋወቅ ያለመ ነው።

ትናንት በተከናወነው የዝግጅቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የፌደራል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የጌዴኦ ዞንና የዲላ ከተማ አመራሮች እንዲሁም በርካታ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ኤክስፖው ዛሬም በተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ጎብኚዎች መጎብኘቱን የሚቀጥል ሲሆን፣ ልዩ ልዩ የኪነ-ጥበብ እና የመዝናኛ ዝግጅቶችን በማካተት እስከ አመሻሹ ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል።

#BunoMalaExpo #Dilla #Gedeo #SouthEthiopia #CoffeeExpo #TourismEthiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1