#Ethiopia | ታዋቂው አሜሪካዊ ድምጻዊ፣ የቢልቦርድ ኮከብ እና የዳንስ ንጉሥ ክሪስ ብራውን ከሃርቨስት ዩኒቨርሲቲ በቪዥዋል እና ፐርፎርሚንግ አርትስ (Visual and Performing Arts) የፒኤችዲ (PhD) ማዕረግ ተቀብሏል።
ይህ የክብር ዶክትሬት ማዕረግ በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ለተንጸባረቀው የረጅም ዓመታት ስኬቱ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፣ አድናቂዎቹም «ዶክተር ብራውን» በማለት የእንኳን ደስ አለህ መልዕክታቸውን እያዥጎደጎዱለት ይገኛሉ።
ክሪስ ብራውን በተለያዩ ጊዜያት በግል ሕይወቱ ካጋጠሙት ውጣ ውረዶች አንጻር ይህንን ማዕረግ ማግኘቱ ለአድናቂዎቹ ትልቅ ድል ተደርጎ ተወስዷል።
በርካታ የዘርፉ ተንታኞች እና የሙዚቃ አፍቃሪያን፣ ድምጻዊው በታሪኩ ያጋጠሙት የሚዲያ ስረዛዎችና ተጽዕኖዎች ባይኖሩ ኖሮ፣ በታዋቂነትና በስኬት ደረጃ ከታላቁ የፖፕ ንጉሥ ማይክል ጃክሰን በላይ ሊገሰግስ የሚችልበት አቅም እንደነበረው በስፋት ይከራከራሉ።
ብራውን ቀደም ሲል በሰጠው አስተያየት፣ የእሱ ብቸኛ ፍላጎት ሙዚቃውን መሥራት፣ እናቱንና ልጆቹን መደገፍ ቢሆንም ዓለም ግን እሱን ለማጥፋትና ለማግለል በተደጋጋሚ እንደሞከረች መናገሩ ይታወሳል።
የደረሱበት ጫናዎችና ጉዳቶች በሙያዊ ጉዞው ላይ የራሳቸውን ጠባሳ ጥለው ቢያልፉም፣ ክሪስ ብራውን ዛሬም ድረስ በሙዚቃው ዓለም ተደማጭነቱን ጠብቆ፣ በትልቅ የስኬት ማማ ላይ መገኘቱን ይህ አዲስ ማዕረግ ዳግም አረጋግጧል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ChrisBrown #DrChrisBrown #HarvestChristianUniversity #MusicNews #GeopoliticsAndCulture #GetuTemesgenMedia
Source: GetuTemesgen









No comments yet.