የሳምንቱ ትልቅ ጨዋታ – አርሰናል ከ ሲቲ

- Advertisement -
Sidebar AD

* ማን ያሸንፋል?

#Ethiopia | በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂው የአርሰናል እና የማንችስተር ሲቲ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ ይደረጋል።

በሳምንቱ አጋማሽ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተጋጣሚዎቻቸውን ያሸነፉት ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ አሸናፊነታቸውን ለማስቀጠል በኢምሬትስ ይጫወታሉ።

ካደረጋቸው አራት የሊግ ጨዋታዎች በአንዱ የተሸነፈው አርሰናል በመከላካሉም በማጥቃቱም አስፈሪ መሆኑን አሳይቷል።

በተለይ በመከላካሉ ይበልጥ ጠንካራ የሆነው አርሰናል የተቆጠረበት አንድ ግብ ብቻ ሲሆን የፊት መስመሩም 9 ግቦችን አስቆጥሯል።

በቶተንሀም እና በብራይተን የተሸነፈው ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ባለፈው ሳምንት የማንችስተር ደርቢን ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

በኧርሊንግ ሀላንድ የሚመራው የሲቲ አጥቂ መስመር ከጠንካራው የመድፈኞቹ ተከላካይ የሚያደርገው ትግል የሚጠበቅም ሆኗል።

አሠልጣኘ ሚካኤል አርቴታ በሰጡት ሐሳብ “ጨዋታውን በማሸነፍ ወጥ ብቃት ላይ እንዳለን ማሳየት እንፈልጋለን” ብለዋል።

የሲቲው አሠልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ “አርሰናል በአሁኑ ሰዓት አውሮፓ ላይ ካሉ ጠንካራ ቡድኖች ቀዳሚው ነው” የሚል ሐሳባቸውን ሰጥተዋል።

በጨዋታው በአርሰናል በኩል ዊሊያም ሳሊባ ከጉዳቱ በመመለሱ በዛሬው ጨዋታ በቋሚነት ሊሰለፍ ይችላል የተባለ ሲሆን ቡካዮ ሳካ አሁንም በማገገም ላይ ይገኛል። የማርቲን ኦዴጋርድ እና ቤን ዋይት መሰለፍ ግን አልተረጋገጠም።

በሲቲ በኩል ደግሞ ኦማር ማርሙሽ አሁንም በጉዳት ከስብስቡ ውጭ ሲሆን ራያን አይቲ ኑሪ እና ጆን ስቶንስ ለጨዋታው ዝግጁ ሆነዋል።

በሌላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በርንማውዝ ከ ኒውካስትል ዩናይትድ እና ሰንደርላንድ ከ አስቶን ቪላ በተመሳሳይ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉም ይሆናል።

በአንተነህ ሲሳይ
#premierleague #arsenal #city #football


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2