“ኢትዮ ሪል እስቴት ካፕ” የእግር ኳስ ውድድር ሊደረግ ነው።

- Advertisement -
Sidebar AD

አርኪ ኤቨንትና የአዲስ አበባ ስፖርት ቢሮ ሪል እስቴት ካፕ ውድድር ለማድረግ የ3 ዓመት ስምምነት ተፈራረሙ።

#Ethiopia | አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር እና ከአዲስ አበባ ስፖርትና ወጣቶች ቢሮ “ኢትዮ ሪል እስቴት ካፕ” የእግር ኳስ ውድድር በጋራ ለማዘጋጀት ስምምነት አድርገዋል።

በስምምነቱ በከተማዋ የስፖርት ቱሪዝምን ለማሳደግ የሚያስችለውን ታሪካዊ የ3 ዓመት የጋራ ስምምነት (MoU) ተፈራርመዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውና ስድስት የሪል እስቴት ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ይህ ውድድር ከፊታችን ግንቦት 15 እስከ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።

ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተብራራው፣ የውድድሩ ዋና ዓላማ መንግስት 300 ታዳጊዎችን ለዓለም እና አፍሪካ ዋንጫ ለማድረስ የያዘውን ፕሮጀክት ለመደገፍና የሪል እስቴት አልሚዎችን ግንኙነት ለማጠናከር ነው።

የአዲስ አበባ ስፖርትና ወጣቶች ቢሮ አማካሪ አቶ ታሪኩ እሸቱ ባለፉት ዓመታት የተገነቡ 400 ስፖርት ማዘውተሪያዎችን ለእንዲህ አይነት ውድድሮች መጠቀም ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል።

የአርኪ ኤቨንት መስራች አቶ ዮሐንስ ግርማ በበኩላቸው ውድድሩ ዘርፉን እንደሚያነቃቃ ጠቁመው፣ የውድድሩ አሸናፊ የክብር ዋንጫ እና የ300 ሺህ ብር የጥቅል ሽልማት፣ ሁለተኛው ደግሞ የ200 ሺህ ብር ሽልማት እንደሚያገኙ አስታውቀዋል።

ፎቶ kebede mekibeb

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: