የኢራን ፓርላማ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለሚገድል ማንኛውም ሰው 50 ሚሊዮን ዩሮ (ወደ 58 ሚሊዮን ዶላር ገደ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኢራን ፓርላማ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለሚገድል ማንኛውም ሰው 50 ሚሊዮን ዩሮ (ወደ 58 ሚሊዮን ዶላር ገደማ) የመንግስት የገንዘብ ሽልማት የሚሰጥ አዲስ የህግ ረቂቅ እያዘጋጀ መሆኑ ታወቀ
ይህ በኢራን ከፍተኛ ህግ አውጪዎች ደረጃ እየተመከረበት ያለው አዲስ የህግ ረቂቅ “የእስላማዊቷ ሪፐብሊክ ወታደራዊ እና የደህንነት ሃይሎች የአረባዊ እርምጃ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፥ መንግስት ለግድያው የተመደበውን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን በይፋ እንዲከፍል የሚያስገድድ ነው።
የኢራን ፓርላማ የብሔራዊ ደህንነት እና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢብራሂም አዚዚ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው እንደተናገሩት፥ ይህ እርምጃ አሜሪካ እና እስራኤል የኢራን ወታደራዊ መሪዎችን እና አዛዦችን ለገደሉበት አጸፋዊ ምላሽ የተዘጋጀ ነው።
አዚዚ አክለውም ዶናልድ ትራምፕ፣ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የአሜሪካ መካከለኛው ዕዝ (CENTCOM) ዋና አዛዥ በዋናነት መገደል እንዳለባቸው ገልጸው፥ ይህንን የግድያ እርምጃ “ሃይማኖታዊ እና ርዕዮተ-ዓለማዊ ተልዕኮ” ሲሉ ጠርተውታል።
ከዚህ መግለጫ አስቀድሞ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በርካታ የኢራን የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች የትራምፕን ግድያ ዘመቻ የሚደግፉ እና ለዚሁ ተግባር የሚውል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ጥሪዎችን የያዙ የጽሑፍ መልዕክቶች ደርሷቸው እንደነበር ተገልጿል።
በተያያዘም በቅርቡ ይፋ የሆኑ የአሜሪካ የስለላ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከኢራን ጋር ግንኙነት አለው የተባለ አንድ ተላላኪ ግለሰብ ትራምፕን ለመግደል በቅድሚያ 5 ሺህ ዶላር ተከፍሎት ሲንቀሳቀስ እንደነበር ተደርሶበታል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1