ከግማሽ ክፍለ ዘመን ( ከ 50 ዓመታት ) በላይ በታማኝነት ያገለገሉት መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ተስፋ ማርያም ከዚህ ዓለም በሞ

- Advertisement -
Sidebar AD

ከግማሽ ክፍለ ዘመን ( ከ 50 ዓመታት ) በላይ በታማኝነት ያገለገሉት መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ተስፋ ማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

#Rthiopia | በቦሬ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ጽኑ ዋርካ በመሆን ለሃምሳ ዓመታት ያህል ያለመታከትና በታላቅ ፍቅር ሕዝበ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ የኖሩት ታላቁ አባት መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ተስፋ ማርያም ሕይወታቸው አልፏል።

አባታችን ለምዕመናን የእምነት ምሰሶ እና የትሕትና ትልቅ አርአያ ነበሩ።

በቅዱስ ሥፍራው ያሳለፏቸው ረጅም ዘመናት ለሥልጣን ወይም ለምድራዊ ዝና ሳይሆን ለእውነተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት የተሰጡ ነበሩ።

ማንኛውንም ዓይነት ፈተናና የሕይወት መከራ ሳይበግራቸው እምነታቸውን ጠብቀው ሐዋርያዊ ሩጫቸውን በድል አጠናቀዋል።

አባታችን በ1977 ዓ.ም መልአከ ገነት የሚለውን የማዕረግ ስም ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት በብፁዕ አቡነ በርተሎሚዎስ አቅራቢነት አግኝተዋል።

ታላቁ አባት በቀድሞው የሲዳሞ ክፍለ ሀገር ውስጥ በይርጋዓለም፣ በጀምጀም፣ በሻኪሶ፣ በነጌሌ ቦረና፣ በዲላ፣ በይርጋጨፌ፣ በአለታ ወንዶ፣ በቦሬ ቅድስት ማርያም እና በይርባ ሙዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሳይቀሩ ቅዱስ ወንጌልን በመስበክና የሰንበት ትምህርት ቤቶችን በማደራጀት ከልጅነት እስከ እውቀት የደከሙ ታላቅ ሐዋርያ ነበሩ።

ለቤተ ክርስቲያን ካበረከቷቸውና ሁልጊዜም በታሪክ ከሚታወሱት ተግባሮቻቸው መካከል
አንደኛው ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያሳዩት ጽናትና ታማኝነት ሲሆን፣ ቅዱስ ስፍራውን ሳይለቁ በቅድስና መኖር የሚቻለው በእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን በተግባር አሳይተዋል።

ሁለተኛው ዕድሜያቸው ቢገፋም መንፈሳቸው እየታደሰ ለምዕመናን መጽናናትና ለአገልግሎት ራሳቸውን አሳልፈው መስጠታቸው ነው።

ሦስተኛው ደግሞ ያከናወኑት መንፈሳዊ ተጋድሎ ሁሉ ያለ ምንም ምድራዊ ጥቅም፣ በቅንነትና በንጹሕ ልብ የተመራ መሆኑ ነው።

በአሁኑ ወቅት አባታችን ከዚህ ዓለም ድካምና መከራ አርፈው ወደማያልፈው የቅዱሳን ማረፊያ ተሻግረዋል።

ምንም እንኳ የአካል መለያየታቸው፣ ያሳደገን፣ የመከረንና ያስተማረን ጣፋጭ ምክራቸውን ማጣታችን ልብን የሚነካ ቢሆንም፣ የሠሩት መልካም ሥራ ግን ሁልጊዜም ሕያው ሆኖ ይኖራል።

ያገለገሏት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያኑ የአባታችንን ጸሎትና በረከት እንዲያገኙ እየተመኘን፣ ለእናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የቦሬ ከተማና የገጠር ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን።

#church #ethiopianorthodox #christianity #memorial #bore #sidamo #orthodox #faith #clergy #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: