#FastMereja I በ“ዜና 24” ዲጂታል ሚዲያ የካሜራ ባለሙያ የሆነው ወጣት ዘመኑ አታላይ፣ በስህተት ወደ ባንክ አካውንቱ የገባለትን 200 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ለባለቤቱ በታማኝነት መለሰ። ወጣቱ ብሩን ለመመለስ በቅድሚያ ብሄራዊ የዲጂታል (ፋይዳ) መታወቂያ ማውጣት ነበረበት።
የካሜራ ባለሙያው ዘመኑ አታላይ በስህተት ወደ ሂሳብ ቁጥሩ የገባውን ይህንን ከፍተኛ ገንዘብ ለባለቤቱ ለማስረከብ በፈለገበት ወቅት፣ የወቅቱን የባንክ አሰራርና መመሪያ ተከትሎ ለመንቀሳቀስ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ማቅረብ ግድ ሆኖበታል። ወጣቱ መታወቂያው ያልነበረው ቢሆንም፣ የሌላውን ሰው ገንዘብ በአስቸኳይ ለመመለስ ሲል የፋይዳ መታወቂያ የመውሰድ ሂደቱን በፈጣን ሁኔታ አጠናቋል።
አስፈላጊውን ህጋዊና የባንክ ፕሮሰስ በሙሉ ካጠናቀቀ በኋላ፣ በአካውንቱ ላይ ተቀምጦ የነበረውን ሙሉ 215 ሺህ ብር ለትክክለኛው የገንዘቡ ባለቤት በዛሬው ዕለት በሰላም አስረክቧል። ድርጊቱ በዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎችና በታዘቡት የባንክ ደንበኞች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል።
Source: FastMereja









No comments yet.