“ኢራን ለስምምነት በጣም ተቃርባለች” – ትራምፕ “ስምምነቱ በአሜሪካ እንደሚነገረው የተቃረነ መግለጫ አይደለም” – እስማኤል ባ…

- Advertisement -
Sidebar AD
“ኢራን ለስምምነት በጣም ተቃርባለች” – ትራምፕ
“ስምምነቱ በአሜሪካ እንደሚነገረው የተቃረነ መግለጫ አይደለም” – እስማኤል ባቃይ

አሜሪካ እና ኢራን የሰላም ስምምነት ለማድረግ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ኢራን ለስምምነት በጣም ተቃርባለች” ብለዋል። “ስምምነቱ ኢራን የኑክሌር መሳሪያ በፍጹም እንዳትጠቀም ይከለክላል” ነው ያሉት።
ትራምፕ “የምንፈልገውን ካገኘን ብቻ የስምምነቱን ፊርማ አስቀምጣለሁ” ሲሉ ገልጸዋል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባቃይ በበኩላቸው “ስምምነቱ የተጠናቀቀው ባለፈው ሳምንት ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ባቃይ “ስምምነቱ በአሜሪካ እንደሚነገረው የተቃረነ መግለጫ አይደለም” ብለዋል።
“እቅዳችን 14 ነጥቦችን ያካተተ ነው” ያሉት ባቃይ “የመጨረሻው ስምምነት ከ30-60 ባሉት ቀናት ውስጥ ይደረጋል” ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኑክሌር ጉዳይ አንዱ የስምምነት አካል መሆኑን በተመለከተ ስለሰጡት አስተያየት “ስለስምምነቱ ይዘት አላውቅም፤ ስለዚያ ምንም አልልም” ብለዋል።
ይሁን እንጂ የኑክሌር እና የሚሳዔል ምርት እንዲሁም የሆርሙዝ ሰርጥ የሁለቱ ሀገራት የስምምነት አካል መሆኑ ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት በኢራን ላይ ሊፈፅሙት የነበረውን ወረራ በሳውዲ አረቢያ፣ ኳታር እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጥያቄ መሰረት መተዋቸውን ገልፀዋል። #bbc #aljazeera
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: