ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር አገራት በኢቦላ ቫይረስ የመጠቃት ስጋት አላቸው‼️
የአፍሪካ ህብረት የጤና ኤጀንሲ ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር አገራት በኢቦላ ቫይረስ የመጠቃት ስጋት እንዳለባቸዉ አስጠነቀቀ።
ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ሩዋንዳንና ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ አስር ሀገራት በኢቦላ ቫይረስ የመጠቃት ስጋት እንዳለባቸው ህብረቱ አስጠንቅቋል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያለውን የኢቦላ ስጋት ወደ ከፍተኛው ደረጃ ከፍ ማድረጉን ተከትሎ፣ የአፍሪካ ህብረት ቫይረሱ 10 አገሮችን ሊያጠቃ እንደሚችል በማስጠንቀቅ ላይ ይገኛል።
ወረርሽኙ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በኢቱሪ ግዛት ሲሆን፤ አካባቢው አስቀድሞም የትጥቅ ግጭቶችና ሰብዓዊ ቀውሶች የሚታዩበት ነው።
በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ቀጥተኛ ወይም የቅርብ ንክኪን ማስወገድ የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስና ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ወሳኝ እርምጃ ነው።
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ፤ እስካሁን በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 82 የተረጋገጡ ህመምተኞች እና ሰባት የሞቱ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ በተጨማሪም ወደ 7መቶ50 የሚጠጉ ኬዞች እና 1መቶ77 በኢቦላ ምክንያት ተከስተዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ ሞቶች እንዳሉ ተገልጿል፡፡
በምስራቅ በኩል ከኮንጎ ጋር የምትዋሰነው ኡጋንዳ አምስት የኢቦላ ተጠቂዎችን አረጋግጣለች።
የአፍሪካ ህብረት የጤና ኤጀንሲ ትናንት ባወጣዉ መግለጫ፤ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ሩዋንዳንና ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ አስር ሀገራት በኢቦላ ቫይረስ የመጠቃት ስጋት እንዳለባቸው አስጠንቅቋል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.