#FastMereja I የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በዘንድሮው የውድድር ዓመት ያስመዘገበው ታሪካዊ ስኬት እና የደጋፊዎቹ ያልተቋረጠ ታማኝነት በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ዘንድ እውቅና እና ሙገሳ እየተቸረው ይገኛል። የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለክለቡ ደጋፊዎች ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት፣ የቡድኑ ጉዞ እንቅፋቶችን አሸንፎ ሕልምን እውን ማድረግ እንደሚቻል ያሳየ ትልቅ ማስተማሪያ መሆኑን ገልጸዋል።
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት በተለይ ደጋፊዎች ላሳዩት ጽናት ትልቅ ቦታ የሰጠ ሲሆን፣ የደጋፊዎቹ ሳይዋዥቁ መቆም ላመኑበት ዓላማ በታማኝነት የመቆም ተምሳሌት መሆኑን አመልክቷል። የጥረት መንገድ በሕመም የተሞላ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ጣፋጭ ድል እንደሚገኝበት የጠቀሱት አቶ ተመስገን፣ የክለቡ ስኬት ትችትና እንቅፋቶች ዓላማን ከማሳካት ሊያግዱ እንደማይችሉ በተግባር ያሳየ መሆኑን አስገንዝበዋል።
Source: FastMereja









No comments yet.