#Ethiopia | የወህኒ አምባ የተሰኘው አዲስ ታሪካዊ ትያትር ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ፍላሚንጎ አካባቢ በሚገኘው የሕፃናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት አዳራሽ ለተመልካች መብቃት ጀምሯል።
በደራሲ መልካሙ ዘሪሁን ተፅፎ በዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ አዘጋጅነት ለክብር መድረክ የበቃው ይህ ተውኔት በምረቃው ዕለት እጅግ ማራኪ እና የተዋጣለት አቀራረብ ለተመልካቾች አሳይቷል።
ይህ ታሪካዊ የጥበብ ስራ ከዝግጅት ጥበቡ ጀምሮ ከማጀቢያ ፊልም (AI ቅንጭብጭቦች) ጋር የተዋሃደበት መንገድ፣ የታሪኩ ጥልቅነት፣ የተዋናዮቹ የትወና ድንቅ ብቃት እንዲሁም የኬሮግራፈር (ዳንስ ውህደቱ) እንዲሁም የመድረክ እነጻ እጅግ የሚደነቅ እንደነበር ተመልካቾች ገልጸዋል።
የተውኔቱ ደራሲ ጸሐፊ ተውኔት መልካሙ ዘሪሁን የትያትሩ አጽመ ታሪክና መቼቱ እንደገለጹት፣ ከ300 እስከ 400 ዓመታት ወደ ኋላ በመመለስ በወቅቱ የነበረውን የአለባበስ፣ የምግብ እና የጸጉር አሰራር ዘይቤ በዝርዝር አጥንቶ በመድረክ ላይ ህያው ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል።
ጎንደር ውስጥ በሚገኘውና በርካታ የኢትዮጵያ ነገስታት ሀገር ለመምራት ሲዘጋጁ ይማሩበት በነበረው ወህኒ አምባ ታሪካዊ ስፍራ ላይ የሚያጠነጥን ነው።
ይህ ታሪካዊ ቦታ ነገስታት የቅስና፣ የድቁና፣ የአካል ብቃት፣ የጦርነት እንዲሁም የህክምና እውቀቶችን የሚቀስሙበት የትምህርት ማዕከል እንጂ የስቃይ ማሰሪያ እንዳልነበረ ታሪኩ በግልጽ ያሳያል።
ይህንን ታላቅ ስራ ወደ መድረክ ለማምጣት ከሰባት ወራት በላይ የፈጀ ሰፊ የታሪክ ምርምርና ዝግጅት ተደርጓል።
አዲሱ ትውልድ የሀገሩን ቀደምት ታሪክ እና አባቶች አገርን ያቆዩበትን ጥበብ ከዚህ የጥበብ ስራ በስፋት እንደሚማርበት ታምኖበታል።
ከዚህ ቀደም ንጉሥ አርማህ እና ህንደኬ የተሰኙ ተወዳጅ ታሪካዊ ተውኔቶችን ለተመልካች ያቀረቡት አዘጋጆች፣ በአሁኑ ወቅት በአዲስ መልክ የተከፈቱት የባህልና ትያትር አዳራሾች መኖራቸው የትያትር ኢንዱስትሪውን በከፍተኛ ሁኔታ እያነቃቃው መሆኑን ጠቁመዋል።
በመጨረሻም መላው ህዝብና የጥበብ አፍቃሪ ይህን አዲስ ቲያትር በመመልከት በታሪኩ እንዲማር፣ እንዲደሰትና እንዲኮራ ጥሪ ቀርቧል።
በዚህ የኪነ ጥበብ ስራ ላይ የረዳት አዘጋጅነት ሚናውን ተስፋዬ ሲማ ሲረከቡ፣ ኤልያስ ደጀኔ፣ ትዕግሥት ዋሲይሁን፣ ራሄል ኤርሚያስ፣ መዓዛ ገብረህይወት፣ ዘቢባ ሀይል፣ ፋሲል ግርማ፣ ያሬድ ኤጉ፣ ኢንስፔክተር መኮንን ምጉሴ፣ ፋአድ መሀመድ፣ ሳሙሶን ግርማ፣ አያሌው ገብረህይወት፣ ፍቃዱ ሳህሌ፣ አሉላ ወንድሙ፣ ከድር ዮናስ፣ ሳሙኤል መስፍን፣ ተፈሪ ደጀኑ፣ መቼልይሽ ታከለ፣ ተመስገን መርሶ እና ሰሎሞን ሞገስን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ተዋንያን የየራሳቸውን ድርሻ በመወጣት ገጸ ባህሪያቱን ህያው አድርገው አቅርበውታል።
#ወህኒአምባ #ታሪካዊቲያትር #ኪነጥበብ #የኢትዮጵያታሪክ #የባህልናቲያትር #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.