የFB Addis ሆቴል 20ኛ አመቱን አክብሯል። በእለቱ The Golden Age የተሰኘ ዘመናዊ ላውንጅ አስመርቋል። የሆቴሉ ባለ

- Advertisement -
Sidebar AD

የFB Addis ሆቴል 20ኛ አመቱን አክብሯል። በእለቱ The Golden Age የተሰኘ ዘመናዊ ላውንጅ አስመርቋል። የሆቴሉ ባለቤት አቶ ኤፍሬም በለጠ ከአስተናጋጅነት በመነሳት ለከፍተኛ ባለሀብትነት የበቁ ኢንተርፕርነር ናቸው።

በታዋቂው «ኤፍሬም ውስኪ» ወይም በሚላቪት ግሮሰሪ ስማቸው የሚታወቁት የሥራ ፈጣሪው አቶ ኤፍሬም በለጠ ንብረት የሆነው ባለ 3 ኮከብ ደረጃው «ኤፍቢ አዲስ ሆቴል» (FB Addis Hotel) 20ኛ አመቱን ሲያከብር በእለቱ በ9ኛ ፎቅ ላይ የሰራውን the golden age ላውንጅን በድምቀት አስመርቋል።ላውንጁ አዲስ አበባን ከፒያሳ 70 ደረጃ ግርጌ ሆኖ 360 ዲግሪ ውበቷን ለመመልከትና ለመዝናናት እድል የሚሰጥ ነው።

ሆቴሉ ወደዚህ ከፍተኛ ደረጃ ከመሸጋገሩ በፊት፣ መሥራቹ አቶ ኤፍሬም በለጠ ከሰው ቤት ተቀጥረው በብርጭቆ ማጠብ ስራ የጀመሩበትን እና ራሳቸውን ችለው የንግድ ፈቃድ ያወጡበትን 20ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ጭምር ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተከናወነ ልዩ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ነው።

ባለ 12 ወለል ሕንጻ የሆነው ኤፍቢ አዲስ ሆቴል ዘመናዊና ሁለንተናዊ አገልግሎቶችን ያካተተ ሲሆን፣ ለዜጎችም ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል። 24 ደረጃቸውን የጠበቁ የመኝታ ክፍሎች አሉት።

ስፖርት ቤት፣ ስቲም ሳውና፣ ሬስቶራንት፣ ባር፣ እንዲሁም በሆቴሉ 9ኛ ፎቅ ላይ ማራኪ ከተማ አቀፍ እይታ (View) ያለው አዲስ የተገነባ ዘመናዊ ላውንጅ (Lounge) ያካትታል።

ከታሪካዊው የደጃችሁ ቤት አካባቢ ጀምሮ መሠረት የጣለበትን የነበረውን የስኪ ቤትና የስኪ ሥራዎች አገልግሎትም በጥራት ማቅረቡን ይቀጥላል። ሆቴሉ በአሁኑ ወቅት ለ62 ቋሚ ሠራተኞች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።

የሆቴሉ ማናጀርና ባለቤት አቶ ኤፍሬም በለጠ እንደገለጹት፣ የዛሬ 20 ዓመት ከሰው ቤት ወጥተው በኪራይ ቤት የጀመሩት ንግድ፤ በአራት የቀበሌ ሱቆች ግዢ አልፎ፣ ከ11 ዓመታት በፊት አካባቢው በልማት ሲፈርስ አሁን ወደሚገኝበት ቦታ ተዛውሯል።

በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ «ኤፍሬም ውስኪ» በሚል ትልቅ ስም ሊገነቡ የቻሉበትን ሚስጥር ሲያስረዱ፣ አስቀድመው ይሠሩበት ከነበረው ቤት የተማሩትንና ያደጉበትን ለንጹህ ነገር የመገዛትና ያለመደራደር እሴት እንደሆነ ገልጸዋል።

ሆቴሉ ዘመናዊ አሠራርና ሲስተም ያለው ቢሆንም፣ አቶ ኤፍሬም ግን አሁንም ያንን የቆየውን፣ ታዋቂው ደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር የጻፈበትን የደጃችሁ ቤት (ውቤ በረሃ) ፍቅር፣ ክብር፣ አንድነትና ማኅበራዊ ትስስር እንዳስቀጠሉበት ይናገራሉ።

በምረቃው ዕለትም የታደሙት ታላላቅ እንግዶች አብረዋቸው የ32 እና የ20 ዓመታት የሕይወት ታሪክ ያላቸው የቅርብ ወዳጆቻቸውና እንደ ቤተሰብ የሚቆጠሩ ደንበኞቻቸው ናቸው።

በመጨረሻም፣ ሆቴሉ ለደረሰበት የዕድገት ደረጃ ዓለም አቀፉ የመጠጥ አምራች ኩባንያ ዲያጆ ላደረገላቸው ዘላቂ የስፖንሰርሺፕና የድጋፍ አጋርነት አቶ ኤፍሬም ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1