መረጃመከላከያ ሠራዊት፣ ሕወሃት እና የኤርትራ መንግሥት በጥምረት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ስጋት የሚፈጥር እንቅስቃሴ ካደረጉ …

- Advertisement -
Sidebar AD
መረጃ‼️
መከላከያ ሠራዊት፣ ሕወሃት እና የኤርትራ መንግሥት በጥምረት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ስጋት የሚፈጥር እንቅስቃሴ ካደረጉ ስለሚወስደው ርምጃ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ማሳወቁን የሠራዊቱ የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ሜ/ጀነራል ተሾመ ገመቹ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
መከላከያ ሠራዊት ይህን ያደረገው፣ “ጽምዶ” የተባለውን የሕወሃትና ኤርትራ “የጸረ-ሉዓላዊነት” ጥምረት ወደ ተግባር ለመቀየር የሚፈልጉ አካላት ካሉ ርምጃው ምን እንደሚኾን የኢትዮጵያ ወዳጆች ማወቅ ስላለባቸው መኾኑን ጀነራሉ ገልጸዋል።
ያም ኾኖ መከላከያ ሠራዊቱ የ”ጽምዶ” እንቅስቃሴን አሁን ባለበት ደረጃ ለኢትዮጵያ “ሰላም” እና “ደኅንነት” አስጊ አድርጎ እንደማይወስደው ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1