በቆዳ ስፋቷ ከኢትዮጵያ ጋር ምትስተካከለው ናሚቢያ 40% መሬቷን ለተፈጥሮ ጥበቃ ከለለች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ናሚቢያ ሀገሪቱ ከጠቅላላ ግዛቷ ውስጥ ከ40 በመቶ በላይ የሚሆነውን መሬት ለተፈጥሮ ጥበቃ የከለለች ሲሆን፣ የአካባቢ ጥበቃና መብትን በሕገ-መንግሥቷ ውስጥ አካትታ ያጸደቀች የመጀመሪያዋ የአፍሪካ ሀገር ናት።

​ሀገሪቱ በዓለም አቀፉ የዘላቂ ቱሪዝም ምክር ቤት መመዘኛዎች መሠረት ወደ 95 በመቶ የሚጠጋ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበች ሲሆን፣ ማኅበረሰብ-ተኮር የዱር እንስሳት ጥበቃ ማኅበራት የዱር እንስሳቱን የመንከባከብ ኃላፊነት ወስደው እየሠሩ ይገኛሉ።

እነዚህ ማኅበራት ከቱሪዝም የሚገኘውን ገቢ በቀጥታ ለአካባቢው ነዋሪዎች በማከፋፈል ረገድም ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ነው።

​ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በተፈጥሮና በባህላዊ እሴቶች ላይ የሚያተኩረው ሥነ-ምህዳራዊ ቱሪዝም በሀገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ይገኛል፤ ይህም በአካባቢው ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት የማያደርሱና ለተፈጥሮ ጥበቃ ትኩረት የሚሰጡ በርካታ ጎብኚዎችን ወደ ናሚቢያ እየሳበ መሆኑ ታውቋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2