የውፍረት መቀነሻ መድሃኒቶች አጠቃቀም ለምን አሳሳቢ ሆነ?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በዴንማርክ የመድኃኒት አምራች ኖቮ ኖርዲክስ ስር የሚገኘው የዌጎቪ እና ኦዜምፒክ የክብደት መቀነሻ መድኃኒቶች የፈጠራ ባለቤትነት መብት አብቅቷል።

ይህም የተለያዩ አገራት የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች መድኃኒቶቹን በመሥራት በርካሽ ለገበያ እንዲያቀርቡ በር ይከፍታል።

ይህም የዋጋ ፉክክር ስለሚፈጥር ዋጋውን ከግማሽ በላይ በመቀነስ ለሕንድ እና ለሌሎች አገራት በፍጥነት ሊዳረስ የሚችልበትን ዕድል ይፈጥራል።

የኢንቨስትመንት ባንኩ ጄፈሪስ ይህንን አጋጣሚ ለሕንድ “አስማታዊ ጊዜ ነው” ሲል ጠርቶታል።

በትክክለኛው ዋጋ እና አጠቃቀም ከተመራ ሴማግሉቲድ የተባለው የክብደት መቀነሳ መድኃኒት የአገር ውስጥ ገበያ አንድ ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተንብይዋል።

ወደ 50 የሚጠጉ የተለያየ የምርት ስያሜ ያላቸው የሴማግሉቲድ መድኃኒቶች በወራት ውስጥ ወደ ገበያ እንደሚገቡ ተንታኞች ይጠብቃሉ።

ይህ አካሄድ ከፍተኛ ፉክክር ባለበት የሕንድ የመድኃኒት ኢንዱስትሪ ውስጥ የተለመደ አሠራር ነው።

ሲታግሊፕቲን የተሰኘው የስኳር በሽታ መድኃኒት በ2022 የፈጠራ ባለቤትነት መብቱን ሲያጣ፣ በአንድ ወር ውስጥ ወደ 30 የሚጠጉ የምርት ስያሜ ያላቸው ወደ ገበያ ሲገቡ ይህ ቁጥር በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ 100 ደርሷል።

በአሁኑ ጊዜ ወደ 60 ቢሊዮን ዶላር የሚገመተው የሕንድ የመድኃኒት ኢንዱስትሪ በ2030 በእጥፍ እንደሚጨምር ይጠበቃል።

ኢንዱስትሪው በአብዛኛው የተገነባው ርካሽ መድኃኒቶችን (ጄኔሪክ) በማምረት ሲሆን አሁን ደግሞ በሴማግሉቲድ ላይ ከባድ ውድድር እንደሚኖር ይጠበቃል።

መጀመሪያ ላይ የስኳር በሽታን ለማከም የተዘጋጁት እነዚህ መድኃኒቶች አሁን ክብደት በመቀነስ ረገድ ጨዋታ ቀያሪ ተደርገው እየተወሰዱ ነው።

ሴማግሉቲድ የምግብ ፍላጎትን እና የደም ስኳርን የሚቆጣጠር ሆርሞንን የመሰለ ሚና ያለው ሲሆን ጂኤልፒ-1 በመባል በሚታወቁ የመድኃኒት ክፍሎች ውስጥ ይመደባል።

መድኃኒቱ የኢንሱሊን ልቀትን በማሳደግ እና የሆድ ባዶነትን በማዘግየት፣ ሰዎች እንዲጠግቡ እና ረዘም ላለ ጊዜ እንዳይራቡ ያደርጋል።

በዓለም ላይ በጣም ከሚፈለጉ የክብደት መቀነሻ ሕክምናዎች መካከል ሆኗል።

በርካታ የሕንድ የመድኃኒት አምራቾች ወደ ሥራ ለመግባት በዝግጅት ላይ ናቸው።

ፋርማክራክ የተባለው የምርም ተቋም ምክትል ፕሬዝዳንት ሺታል ሳፓሌ እንደገለጹት ከሆነ ሲፕላ፣ ሰን ፋርማ፣ ዶ/ር ሬዲስ ላቦራቶሪስ፣ ባዮኮን፣ ናትኮ፣ ዚደስ እና ማንዳይማርክ ፋርማ ያሉ ዋና ዋና ኩባንያዎች የታወቁ ጄኔሪክ መድኃኒቶችን እያዘጋጁ ሲሆን፣ ብዙዎቹም ተመሳሳይ እርምጃ የመውሰድ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።

ዋጋውም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ይጠበቃል።

አሁን ያለው ወርሃዊ የሕክምና ወጪው ከፍተኛ ነው።

ኦዜምፒክ ከ95 አስከ 119 ዶላር ይሸጣል።

ዌጎቪ ደግሞ ከ108 አስከ 173 ዶላር ሊያወጣ ይችላል።

ውድድሩ ሲጠናከር ወርሃዊ ዋጋው ከ36 አስከ 54 ዶላር እንደሚወርድ ይጠበቃል።

ዝቅተኛ ዋጋ ሲኖር ደግሞ ገበያውን ሊለውጠው ይችላል።

ዋጋ መቀነሱን ተከትሎ መድኃኒቶቹን ያለአግባብ የመጠቀም ስጋቶች አሉ።

ታካሚዎች በአካል ብቃት አሠልጣኞች፣ በውበት ክሊኒኮች ወይም ይህን ለማድረግ ሥልጣን በሌላቸው የምግብ ባለሙያዎች ከፍተኛ መጠን እንደሚሰጣቸው ሐኪሞች ሪፖርት ያደርጋሉ።

የበይነ መረብ ፋርማሲዎችም አንዳንድ ጊዜ መድኃኒቶቹን ከተወሰነ ምክር በኋላ ይሸጡታል።

የውበት ባለሙያዎች ለሰርግ ወይም ለማኅበራዊ ዝግጅቶች ፈጣን የሰውነት መቀነሻ “ጥቅሎችን” ማስተዋወቅ ጀምረዋል።

ርካሽ መድኃኒቶች በስፋት ሲገኙ እንዲህ ያሉ ልማዶች ሊስፋፉ ይችላሉ።

“ርካሽ መድኃኒቶችን በብዛት ማግኘት ማለት የአላግባብ አጠቃቀም ዕድልን ይጨምራል” ይላሉ መቀመጫቸውን በሙምባይ ያደረጉት የደረት ሐኪም ባሁሚክ ካምዳር።

“ተጨማሪ ኃላፊነትን እና ጥብቅ ቁጥጥርን ይጠይቃል።

በእነዚህ መድኃኒቶች ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት ተስፋ አለኝ።”

ይህ ማስጠንቀቂያ ላክዳዋላ ስለምርት ደረጃዎች ያላቸውን ስጋት የሚያስተጋባ ነው።

#የክብደትመቀነሻ #መድሃኒት
#ፋርማሲ #BBC #ቤልጂየም
#ጌጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemsgen #Mediacommunication


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1