የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲው” ኮሶበር በር” ህንፃ ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | “ኮሶበር በር” እንጅባራ ዩኒቨርስቲ በ2018 ዓ.ም ሲያከናውናቸው ከቆዩት የግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው።

በዛሬው ዕለት ግንባታው ተጠናቆ የተመረቀው “ኮሶበር በር” የአካባቢውን ታሪክ፣ባህል እና እሴት ብሎም “የኢትዮጵያን ታሪክ ያካተተ ኪነ ህንፃ መሆኑ ተገልጿል።

ከታሪካዊው የላሊበላ ኪነ ህንፃ በርካታ ጥበቦች እና ታሪኮችን የያዘም ነው።

ዩኒቨርሲቲው የጀመረውን በመጨረስ በተግባር እያስመሰከረ ያለ ተቋም መሆኑን በምረቃ ስነስርዓቱ የተገኙ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው የአካባቢው ተምሳሌት ከመሆን አልፎ የክልሉ ልዩ ምልክት ሆኗል ያሉት ሀላፊዎቹ ቀጣይም ለሁለንተናዊ ለውጡ አብረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።

“የኮሶበር በር “የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ተጨማሪ አርማው( ምልክቱ) መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ.ር) ተናግረዋል።

በዚህ ትልቅ ፕሮጀክት ለተሳተፉ ሁሉ ፕሬዝዳንቱ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1