በ11 የምርጫ ክልሎች የድጋሜ ምርጫ እንዲደረግ በቦርዱ ተወሰነ።

- Advertisement -
Sidebar AD

አምስቱ የምርጫ ክልሎቹ በሶማሌ ክልል የሚገኙ መሆናቸዉን ቦርዱ ይፋ እያደረገ ባለዉ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዉጤት ማሳወቂያ መርሃ ግብር ላይ ተገልፆል።

ሀማሬ፥ ዳራቶሬ፥ ሀርገሌ፥ ባቱ ዝዋይ፥ ቤጊ፥ አርሆሳ፥ ጨንቻ፥ ሶሮ 1፥ ጠንባሮ ፥ ሀደካላ፥ ሀደካለ ምርጫ ክልሎች የድጋሜ ምርጫ ይደረግባቸዋል ተብሏል።

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ሶሬ1 እና ጠምባሮ ምርጫ ክልሎች ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የድጋሜ ምርጫ ይደረግላቸዋል።

ሀርገሌ ፥,ዳሮር፥ ሀደካላ ፥ ሀማሬ እና ዳራቶሬ የተባሉ በሶማሌ ክልል የሚገኙ የምርጫ ክልሎች የድጋሜ ምርጫ ያደርጋሉ።

ባቱ ዝዋይ እና ቤጌ ምርጫ ክልሎች በኦሮሚያ ክልል ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክርቤት የድጋሜ ምረጫ የሚደረግበት ይሆናል ተብሏል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ጨንቻ ምርጫ ክልል ለክልል ምክርቤት የድጋሜ ምርጫ ይካሄዳል።

ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም ነው!


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: