መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና ቱሪዝም ዙሪያ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ ሊያካሂድ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ሮቤ – በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የሚገኘው መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ትምህርት ዘርፍ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሚናን የሚመለከት ሁለተኛውን ዙር ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ ከሰኔ 15 እስከ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

“Reimagining Tourism and Hospitality Education through Artificial Intelligence: Building Future-Ready Skills, Innovation Capacity, and Ethical Human-Centered Practice” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ኮንፍረንስ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የመጡ ቁልፍ ተናጋሪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ ምሁራን እና ተሳታፊዎችን ያሳትፋል።

እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ ኢንዶኔዢያ፣ ሩሲያ፣ ካሜሩን እና ሌሎች ሀገራት ተሳታፊዎች እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ ደግሞ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከመንግስት ተቋማት እና ከቱሪዝም ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች ይሳተፋሉ።

በኮንፍረንሱ ወቅት ዘመናዊ የምረቃ አዳራሽ ምረቃ፣ በውጭ አጋሮች ድጋፍ የተገነባ አዲስ የዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ (Website) ምረቃ እና ሌሎች ተቋማዊ መርሃ ግብሮች እንደሚከናወኑም ተጠቁሟል።

ከ430 ኪሎ ሜትር በላይ ከአዲስ አበባ ርቀት ላይ የሚገኘው መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በ1999 ዓ.ም. የተመሰረተ ሲሆን በሮቤ፣ ጎባ እና ሻሸመኔ ካምፓሶች በመዋቀር 52 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 58 የማስተርስ እና 6 የዶክትሬት መርሃ ግብሮችን እያስተማረ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ከ46 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በማስመረቅ ለአገሪቱ ልማት አስተዋፅኦ እያደረገ ሲሆን በትምህርት፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች ያለውን ሚና እያጠናከረ መሆኑን ገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ኮንፍረንሱን በአካል ወይም በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮቹ እንዲከታተሉ ለምሁራን፣ ለተማሪዎች እና ለህዝብ ጥሪ አቅርበዋል።

#MaddaWalabuUniversity #AI #Tourism #Hospitality #Conference #Robe #EthiopiaNews #Education #Innovation #MWU


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2