በእምነት ተቋም ውስጥ በመግባት ውድመትና ዝርፊያ የፈጸሙ 21 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

- Advertisement -
Sidebar AD

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ሠዓት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው አያት 49 ቁጥር-2 የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒም) አካባቢ ነው።

በተጠቀሰው አካባቢ የሚገኝው ባዶ ቦታ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የመንግስተ ሰማይ እንደራሴዎች ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የተወሰነ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑም ግንባታ አድርጎ አገልግሎት እየሠጠበት ይገኛል።

ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ሠዓት ላይ ቁጥራቸው 21 የሆኑ የጋራ መኖሪያ መንደሩ ነዋሪዎች በቡድን በመደራጀትና ቦታው የእኛ ነው በማለት የቤተክርስቲያኑን ግቢ በኃይል ሰብረው በመግባት 10,132000 (አስር ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ) ብር የሚገመት ንብረት የመዝረፍና የማውደም ወንጀል ፈጽመዋል።

የወንጀል ድርጊቱ መፈጸም መረጃ የደረሰው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያም በወንጀሉ ተሳታፊ የሆኑ ግለሠቦች ምንም እንኳን ከአካባቢው ቢሠወሩም ከያሉበት በቁጥጥር ስር ውለው ተገቢው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።

በቀጣይ በወንጀሉ ተሳታፊ ናቸው ያላቸው ግለሠቦች ላይ ክስ እንደሚያስመሠርት የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሠል ድርጊቶች የኃይማኖት ግጭት የሚቀሰቅስና ተከባብሮ የኖረውን ህዝብ በጥርጣሬ እንዲታይ የሚያደርግ በመሆኑ ሁሉም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባውም አሳስቧል።






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: