በእምነት ተቋም ላይ ጥቃትና ዝርፊያ የፈጸሙ 21 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ለበአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ የእምነት ተቋም ላይ በኃይል በመግባት ከፍተኛ የንብረት ውድመትና ዝርፊያ የፈጸሙ 21 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ላይ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው አያት 49 ቁጥር-2 የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) አካባቢ መሆኑ ታውቋል።
ጥቃት የደረሰበት ስፍራ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ውሳኔ መሰረት ቦታ ተሰጥቶት፣ ግንባታ ተከናውኖበት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው “ የመንግስተ ሰማይ እንደራሴዎች ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን» መሆኑ ታውቋል።
ቁጥራቸው 21 የሚሆኑ የጋራ መኖሪያ መንደሩ ነዋሪዎች በቡድን በመደራጀት “ቦታው የእኛ ነው” በሚል ሰበብ የቤተክርስቲያኑን ቅጥር ግቢ በኃይል ሰብረው በመግባት ጥቃቱን ፈጽመዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በፈጸሙት የጋራ ዝርፊያና ውድመት በግምት 10 ሚሊዮን 132 ሺህ (10,132,000) ብር የሚያወጣ ንብረት ማውደማቸውና መዝረፋቸው ተገልጿል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.