አንዲ በርንሃም በሚፋጀው ወንበር ይቀመጡ ይሆን?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ስታርመር ስልጣናቸውን መልቀቃቸው፣ በታላቋ ብሪታኒያ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ ሰባተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሾሙ የሚያደርግ ነው።

ይህም በሀገሪቱ እየታየ ያለውን ከፍተኛ የፖለቲካ አለመረጋጋት እንዲጎላ አድርጎታል።

ስታርመር ከስልጣን መልቀቃቸውን ሲያበስሩ፣ ፓርቲያቸውን ለቀጣዩ አጠቃላይ ምርጫ ለመምራት በቂ ድጋፍ እንደሌላቸው በመገንዘብ ውሳኔውን በክብር መቀበላቸውን ገልጸዋል።

ከስልጣን በኋላም ለቤተሰባቸው ትኩረት እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

ስታርመር አዲሱ የፓርቲው መሪ እስኪመረጥ ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ይቆያሉ።

የሌበር ፓርቲ አዲስ መሪን ለመምረጥ የሚያስችለውን የምርጫ ሂደት ከሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. (July 9) ጀምሮ እንደሚያካሂድ ተገልጿል።

አንዲ በርንሃም ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚወዳደሩ በይፋ ያረጋገጡ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የፓርቲው ዋና ተመራጭ ሆነው እየታዩ ይገኛሉ።

ሌላ ተወዳዳሪ ካልቀረበ፣ በርንሃም በሐምሌ ወር አጋማሽ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቀድሞ የግሬተር ማንቸስተር ከንቲባ የነበሩት አንዲ በርንሃም ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ በማሸነፍ ወደ ፓርላማ ተመልሰዋል።

ይህ ድል በፓርቲው ውስጥ ለውጥ ለሚፈልጉ አባላት ትልቅ መነሳሻ ሆኗል።

የሌበር ፓርቲ አዲሱን መሪ ለመምረጥ የሚያስችለውን ሂደት በሐምሌ ወር የሚጀምር ሲሆን፣ የፓርላማው የበጋ እረፍት ከመጀመሩ በፊት አዲሱ መሪ እንደሚመረጥ ይጠበቃል።

አንዲ በርንሃም ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታው ትክክለኛ ሰው መሆናቸውን በርካቶች እየተናገሩ ይገኛል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Britain #Starmer #Polticalturmoil
#Andiburnham
#ጌጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemesgen #Mediacommunication


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: