በኳታር የጋዝ ማቀነባበሪያ ተቋም ፍንዳታ 13 ሰዎች ሞቱ፣ 66 ቆሰሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኳታር የሚገኝ አንድ የጋዝ ማቀነባበሪያ ተቋም ላይ በደረሰ ፍንዳታ 13 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ፣ 66 ሰዎች መቁሰላቸውን የኳታር ኢነርጂ ሚኒስትር ሳድ አል-ካዓቢ ገለጹ።

ሚኒስትሩ እንዳሉት፣ አደጋው በተቋሙ ውስጥ ከተከሰተ ፍንዳታ የተነሳ ሲሆን፣ የሟቾችና የተጎዱት ቁጥር በይፋ ተረጋግጧል።

ሆኖም ፍንዳታው በኳታር የተፈጥሮ ጋዝ ምርትና ወደ ውጭ ሀገራት የሚደረገውን የጋዝ ላኪነት ሥራ እንደማይስተጓጎል አረጋግጠዋል።

የአደጋው መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን፣ ባለሥልጣናት በተጎዱ ሰዎች ላይ የሕክምና እና የእርዳታ ሥራዎችን በማጠናከር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

#Qatar #GasPlant #Explosion #Energy #News #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: