አሜሪካ : ከ300 በላይ ድሮኖችን በቁጥጥር ስር ዋሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአሜሪካ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ (FBI) እና ሌሎች የፌዴራል ደህንነት ተቋማት ከ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ውድድር መጀመር ጀምሮ በውድድሩ ስታዲየሞችና የደጋፊዎች መሰብሰቢያ ስፍራዎች አካባቢ ያለፍቃድ ሲበሩ የተገኙ ከ300 በላይ ድሮኖችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ።

ተቋማቱ እንዳሉት እርምጃው የተወሰደው ከትራንስፖርት ደህንነት አስተዳደር (TSA) እና ከሌሎች የደህንነት አካላት ጋር በመተባበር በተካሄደ የአየር ክልል ጥበቃ ዘመቻ ነው።

በዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች በሚካሄዱባቸው ቀናት በስታዲየሞች ዙሪያ በ3 ኖቲካል ማይል ራዲየስ እና እስከ 3,000 ጫማ ከፍታ ድረስ ማንኛውም የአየር ተሽከርካሪ ወይም ድሮን መብረር ተከልክሏል።

እንዲሁም በደጋፊዎች ፌስቲቫሎችና መሰብሰቢያ ቦታዎች ዙሪያ በ1 ኖቲካል ማይል ራዲየስ የበረራ እገዳ ተጥሏል። ይህን ጊዜያዊ የበረራ ክልከላ (TFR) የጣሱ ድሮኖች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑ ተገልጿል።

በቴክሳስ ግዛት በሚገኘው AT&T Stadium ብቻ 39 ድሮኖች የበረራ ክልከላውን በመጣስ መያዛቸው ተገልጿል። በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ጥሰቶች መመዝገባቸው ተነግሯል።

ባለሥልጣናቱ እንዳስጠነቀቁት፣ በተከለከሉ የአየር ክልሎች ውስጥ ያለፍቃድ ድሮን የሚያበሩ ግለሰቦች ድሮናቸው ሊወረስ እንደሚችል፣ በወንጀል ክስ ሊጠየቁ እንደሚችሉ እና እስከ 100,000 ዶላር የሚደርስ ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችል ገልጸዋል።



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: