የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት

- Advertisement -
Sidebar AD

በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

#Ethiopia | የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ አዲስ ከፍተኛ ኃላፊነት ተሰጣቸው።

ፕሬዝደንቷ የተመደቡት በምእራብ አፍሪካና ሳህል ቢሮ ውስጥ ገለልተኛ ስትራቴጂያዊ ግምገማ እንዲያደርጉ ሲሆን፣ ዋና ተግባራቸውም ተቋሙ ለአካባቢው ቀውሶች በሚሰጠው ዘገምተኛ ምላሽ ሳቢያ የሚነሱበትን ትችቶችና የአሰራር ክፍተቶች መመርመር ነው።

ይህንን ከባድ አህጉራዊ አደራ ለመወጣት የያዝነው የሰኔ ወር እንደተጠናቀቀ በቀጥታ ወደ ስራ ይገባሉ።

ወይዘሮ ሳህለወርቅ ስራቸውን ከመጀመራቸው በፊት በመጀመሪያ ወደ ኒውዮርክ በማቅናት ከፀጥታው ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ የሚቀበሉ ሲሆን፣ በመቀጠልም የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ወደሚገኝበት ሴኔጋል ዳካር በመጓዝ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ይወያያሉ።

ለቀድሞዋ ፕሬዝደንት ይህ ታላቅ ኃላፊነት ሊሰጣቸው የቻለው ቀደም ሲል በሴኔጋል፣ ማሊ፣ ጊኒና ኬፕ ቨርዲ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ባገለገሉበት ወቅት ስለ ቀጠናው ባካበቱት የላቀ እውቀትና ሰፊ ግንዛቤ መሆኑ ተገልጿል።

#SahleWorkZewde #UN #Ethiopia #WestAfrica #BreakingNews


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: