ከጅቡቲ የጫነውን ነዳጅ አፋር ላይ ሲቀሽብ የነበረው አሽከርካሪ እጅ ከፍንጅ ተያዘ
ከጅቡቲ የተጫነ ነዳጅን በሕ-ገወጥ መንገድ በመቀሸብ ላይ የነበረ የነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪ በአፋር ክልል የፀጥታ ሃይሎችና በንግድ ቢሮ በተደረገ ክትትል እጅ ከፍንጅ መያዙን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል ።ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ነዳጅን ለማሠራጨት የተጣለበትን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተውና የግል ጥቅምን በማስቀደም ጅቡቲ የጫነውን ነዳጅ በሕ-ገወጥ መንገድ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲል የቀሸበው ግለሰብ መያዙን ባለስልጣኑ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ይፋ አድርጓል ።
ሃላፊነት በጎደላቸው ግለሰቦች የሚፈጸሙ መሠል ተግባራት በነዳጅ ስርጭት ላይ ከሚያደርሱት መስተጓጎል በተጨማሪ የቀሸቡትን ነዳጅ በሕገ-ወጦች በኩል በውድ ዋጋ በመሸጥ በህብረተሰቡ ላይ ጫናን ይፈጥራሉ።በመሆኑም ግለሰቦቹ ለነዳጅ ብክነትና ለአደጋ ተጋላጭነት የሚዳርግ ተግባርን በቸልተኝነት እየፈፀሙ መሆኑ ተነግራል፡፡
ይህን ጥፋት በሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚደረገው ክትትልና የእርምት እርምጃ በፀጥታ አካላት፣በክልል ንግድ ቢሮዎችና በባለስልጣን መስሪያቤቱ በኩል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተቋሙ አሳስቧል፡፡
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.