ቅዱስ ገብርኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፣ የልባችንን መልካም መሻትም ይሙላልን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ500 ዓመተ ዓለም ግንቦት 10 ቀን የእረፍታቸው መታሰቢያ ሲሆን፣ በየዓመቱ ታሕሣስ 02 ደግሞ ዓመታዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡ በትንቢተ ዳንኤል ታሪካቸው በሰፊው ተጽፎ የሚገኘው “ሠለስቱ ደቂቅ” ወይም ሦስቱ ሕፃናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል የባቢሎኑ ንጉስ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ባጠፋት ጊዜ ማርኮ ከወሰዳቸው እስራኤላውያን ውስጥ ይገኙበታል፡፡

በንጉሱ ቤት እንዲቀመጡ ከተመረጡት ምርኮኞች ውስጥም እነዚህ የይሁዳው ንጉስ የኢዮአቄም ልጆችና ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የሀገራቸው ነገር ዘወትር ያሳስባቸዋልና በጾምና በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ እናም በቤተ መንግስት ከሚዘጋጀው ምግብ ይልቅ ጥራጥሬ መብላት ነበር የመረጡት፡፡ በንጉሱ ፊት የሚቀርቡብት ቀን ሲደርስም ከሌሎቹ ሕፃናት ይልቅ ወዝተውና አምረው ይታዩ ነበር፡፡ በቤተ መንግስቱ ከሚኖሩ ወጣቶችና ከባቢሎናውያን ወገንም የእነርሱን ያህል ጥበበኛ አልተገኘም፡፡
ንጉስ ናቡከደነጾርም ወዷቸዋልና በአማልክቱ ስም ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ብሎ ሰየማቸው፡፡ ይህ በንጉሱ ዘንድ ያገኙት ተቀባይነት በባቢሎናውያኑ የቤተ መንግስቱ ሰዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅናት ፈጠረ፡፡ እናም ነገር መጎንጎን ጀመሩ፡፡

ንጉሱ ለክብሩ መገለጫ ቁመቱ 60 ክንድ የሆነ የወርቅ ምስል አቁሞ ሕዝቡን ሁሉ እንዲያሰግድ፣ የማይሰግድ ቢኖር እስከ ሞት በሚደርስ ቅጣት እንዲቀጣ ምክር አቀረቡና አስተገበሩት፡፡ ሦስቱ ሕጻናት ግን ለመስገድ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ፡፡
ይህን ጊዜም በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ተፈረደባቸው፡፡ 49 ክንድ የሆነ እሳት ነዶም ወደዚያ ተጣሉ፡፡ እነርሱ ግን በእሳቱ ውስጥ ሆነው አምላካችን እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፡፡ በዚህ መካከል ንጉሱ በእሳት ውስጥ አራት ሰዎች እየተመለከተ እንደሆነ ገለጸ፡፡
አራተኛው ሊያድናቸው የመጣው ሊቀ ማላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ነበር፡፡ ከልብሳቸው አንዲት ክር፣ ወይም ከጸጉራቸው አንዲት ነቁጥ ሳትቃጠል ወጥተዋል፡፡ ወደ እሳቱ የጣሏቸው ሰዎች ግን በወላፈኑ ተለብልበው ሞተዋል፡፡
አስገራሚው ነገር ንጉሱ ናቡከደነጾር እጅግ ይወዳቸው ነበርና ሲሞት በመካከላቸው እንዲቀብሩት ትዕዛዝ በማስተላለፉ በእነርሱ መቃብር ነው የተቀበረው፡፡

አሁን በዘመናችንም ዓለምና አምሮቷን ንቀው፣ በገዳማትና በየዋሻው ያሉ አባቶቻችን በቀን አንድ ጊዜ መናኛ ነገር እየተመገቡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው ጸንተው የሚኖሩት፡፡ የበረከታቸው ማሳያ የሆነው ደግሞ የጸሎታቸው ኃይል ነው፡፡ ድውያን ይፈወሳሉ፣ ተአምራት ያደርጋሉ፡፡ እነዚህን ገዳማት በመደገፍና በዓታቸውን በማጽናት የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: