#Ethiopia | የቦሊዉድ ታዋቂው ተዋናይ አክሻይ ኩማር ባለቤቱ ትዊንክል ኻና በሥራዎቹ ላይ እጅግ ጥብቅና ቀጥተኛ ትችት የምትሰነዝር ቀዳሚ ተቺው መሆኗን ተናገረ።
ተዋናዩ “ዌልካም ቱ ዘ ጃንግል” የተሰኘውን አዲስ ፊልሙን በማስተዋወቅ ላይ በነበረበት ወቅት በሙያዊም ሆነ በግል ሕይወቱ ውስጥ ከማንም በላይ የእሷ አስተያየት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠውና የእሷ ግልጽ ምላሽ ሁልጊዜም መሬት እንዲረግጥ እንደሚያደርገው ገልጿል።
በቅርቡ ከቦምቤይ ታይምስ ላውንጅ ጋር ባደረገው ቆይታ በጣም አስቸጋሪው ተቺህ ማን ነው ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ያለምንም ማንገራገር የሕይወት አጋሩን ስም የጠራው አክሻይ የእሷን የትችት ደረጃ በሳቅ የታጀበ ማብራሪያ ሰጥቶበታል።
ባለቤቱ በሥራዎቹ ላይ የምትሰጠውን አስተያየት “እጅግ ጨካኝ” ሲል የገለጸው አክሻይ ኩማር ”እሷ ጨካኝ ስትሆን ወሰን የላትም፤ በማንኛውም ጊዜ በትችቷ ልትገድለኝ ትችላለች እሷ ፊት ምንም መከላከያ የለህም” በማለት ሁኔታውን አስረድቷል። ይሁን እንጂ በቅርቡ ያጋጠመውና እጅግ ያስደሰተው አንድ ያልተጠበቀ ክስተት መኖሩን አልሸሸገም።
”ባለቤቱ ወዳሴ አታበዛም’ ‘፤ለሌላ ፊልሙ ድምፅ በመቅረጽ ላይ እያለ ባለቤቱ ትዊንክል አዲስ ለሚወጣው ፊልሙ ማስታወቂያ ያላትን አድናቆት የገለጸችበትን መልዕክት እንደላከችለት ተናግሯል።
ይህ ከእሷ እምብዛም የማይገኝ ብርቅዬ መወድስ በመሆኑ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ለፊልም ዳይሬክተሩ ጭምር “ባለቤቴ የፊልሙን ማስታወቂያ እንደወደደችው መልዕክት ስለላከችልኝ ዛሬ በጣም ደስተኛ ነኝ” በማለት ገልጾለታል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.