ሰበር ዜናየአሜሪካ ኤምባሲ ለሕወሓት ማስጠንቀቂያ ሰጠ!የአሜሪካ ኤምባሲ በትግራይ ክልል ያለውን ችግር ለመፍታት እየተካሄዱ ያሉ …

- Advertisement -
Sidebar AD
ሰበር ዜና
የአሜሪካ ኤምባሲ ለሕወሓት ማስጠንቀቂያ ሰጠ!
የአሜሪካ ኤምባሲ በትግራይ ክልል ያለውን ችግር ለመፍታት እየተካሄዱ ያሉ የሰላም ሂደቶችን “የሚያደናቅፉ” አካላት፤ በአፍሪካ ህብረት ለሚመራው የውይይት ጥረት “በአስቸኳይ ትብብር” እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
የፖለቲካ መሪዎች የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነትን “ሙሉ ለሙሉ” ተግባራዊ ማድረጋቸው “እጅግ አስፈላጊ” መሆኑንም ኤምባሲው ገልጿል።
ኤምባሲው ይህን የገለጸው፤ በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ በቃል አቃባዩ በኩል ዛሬ አርብ ሰኔ 19፤ 2018 ባወጣው መግለጫ ነው።
የዛሬው መግለጫ፤ አሜሪካ “አክራሪ” ባለቻቸው የህወሓት አባላት እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ ገደብ መጣሏን ካሳወቀች ከአንድ ሳምንት በኋላ የወጣ ነው።
የዛሬው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ ህወሓትን በቀጥታ ባይጠቅስም፤ “ሆነ ብለው” የሰላም ሂደቶችን “የሚያደናቅፉ” አካላት የሚል አገላለጽ ተጠቅሟል። በክልሉ ያሉ የፖለቲካ እና የሲቪል ማህብረሰብ መሪዎችም፤ “በፖለቲካዊ ውይይት” መሳተፍ እንደሚገባቸውም ኤምባሲው በመግለጫው አሳስቧል።
መሪዎቹ በጥቅምት 2015 በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመውን የግጭት ማቆም ስምምነት “ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ” ማድረጋቸው “እጅግ አስፈላጊ” መሆኑንም ኤምባሲው አስገንዝቧል።
አሜሪካ ይህን ብትልም የትግራይ ክልልን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደረ ያለው ህወሓት፤ የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት “መፍረሱን” በተደጋጋሚ በሚያወጣቸው መግለጫዎች ሲያስታውቅ ቆይቷል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2