#Ethiopia | በሀገሪቱ የታወቁ አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ተማሪዎችን በ2018 ዓ.ም የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘት አስመርቀዋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኪነጥበብ ባለሙያዎች ከተመራቂዎች፣ ከቤተሰቦቻቸው፣ ከመምህራን እና ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ባለሙያዎቹ በተለይ ከዘንድሮ የቴአትር ጥበባት ተመራቂዎች ጋር በአንድ መድረክ መገኘታቸው፣ ወጣቶቹ በጥበብ ዘርፍ የተሻሉ ሥራዎችን ለማበርከት የሞራል ስንቅና መነሳሳት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም በጥበብ ለሀገርና ለሕዝብ ማገልገል የሚያስገኘውን ክብርና እውቅና ተመራቂዎቹ በተግባር ማየታቸው ወደ ሙያ ዓለም በሚገቡበት ጊዜ ከፍተኛ መነሳሳት እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።
በአርቲስት ወይንሸት አበጀ እና በአርቲስት አሸናፊ ማህሌት አስተባባሪነት፣ እንዲሁም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋባዥነት የተካሄደው መርሃ ግብር በቀጣይም የኪነጥበብ ባለሙያዎች ለሀገርና ለማኅበረሰብ በሚጠቅሙ ተግባራት ላይ ይበልጥ እንደሚሳተፉ ተስፋ ተጥሎበታል።
የክብር እንግዶቻችንን እናመሰግናለን!
– የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኪነጥበባት ሳይንስ ምሩቃን
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኪነጥበባት ሳይንስ ምሩቃንን ለማክበርና በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመታደም ከአዲስ አበባ የመጡት የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ልዑካን አባላት ዩኒቨርሲቲያችንን በደመቀ ሁኔታ አግኝተውታል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲያችን በሲኒማና ቴአትር፣ በሙዚቃ፣ በስነ-ጽሁፍ እንዲሁም በሥዕልና ቅርጻቅርጽ ጥበባት ዘርፎች ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ የሚገኝ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት በሥዕልና ቅርፃቅርጽ እንዲሁም በሲኒማና ቴአትር ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በልዩ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል።
በዚህ ደማቅ የታሪክ ምዕራፍ ላይ በቦታው በመገኘት፣ ለምሩቃኑ ያላቸውን አክብሮትና ድጋፍ ላሳዩት ለተከበሩና ለተወደዱ አርቲስቶቻችን ዩኒቨርሲቲው የላቀ ምስጋናውን ያቀርባል ሲሉ አወድሷቸዋል።
አርቲስት ኃይሉ ፀጋዬ
አርቲስት ደረጀ ኃይሌ
አርቲስት አበበ ተምትም
አርቲስት ተስፉ ብርሃኔ
አርቲስት ተሻለ ወርቁ
አርቲስት እታፈራሁ መብራቱ
አርቲስት ፍቃዱ ከበደ
አርቲስት ዮሐንስ ተፈራ
አርቲስት አቤል ሰለሞን
አርቲስት ዳንኤል ወርቁ
አርቲስት በፍቃዱ አባይ
አርቲስት ወይንሸት አበጀ
አርቲስት አሸናፊ ማህሌት
አርቲስት ፍሬወይኒ ገብረፃዲቅ
አርቲስት ራኬብ በቀለ
የኪነ-ጥበብ ባለውለታዎችና አንጋፋ ባለሙያዎች በምሩቃኑ መካከከል መገኘታቸው ለነገዎቹ የጥበብ ሰዎች ትልቅ ብርታት፣ ለተቋማችንም ከፍተኛ ክብር ሲሉ ተደምጠዋል።
ለኪነጥበብ ሳይንስ ምሩቃን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!



Source: GetuTemesgen









No comments yet.