“የፌዴራል መንግሥት የትግራይን ሕዝብ ሊያድን ይገባል!”የሕወሃት ፅንፈኛ ቡድን ከዚህ ቀደም ያደርገው ከነበረው የወርቅ ንግድ በ…

- Advertisement -
Sidebar AD
“የፌዴራል መንግሥት የትግራይን ሕዝብ ሊያድን ይገባል!”
የሕወሃት ፅንፈኛ ቡድን ከዚህ ቀደም ያደርገው ከነበረው የወርቅ ንግድ በአሁኑ ወቅት የትግራይ ወጣቶችን ወደ መሸጥና ወደ ማገት መሸጋገሩን የወለዶ ትግራይ ፖለቲካ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ጉዕሽ ግደይ ገለጹ።
ቡድኑ ታሪካዊውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተግባር በማፍረስና ከሀገር ውጭ ካሉ ጠላቶች ጋር “ፅምዶ” በሚል ስያሜ በመተባበር ለሌላ ጦርነት እየተዘጋጀ እንደሚገኝና በትግራይ ክልል ሁሉንም ሰላማዊ የፖለቲካ መንገዶች ዘግቶ በጉልበት እያስተዳደረ መሆኑን አስረድተዋል። የትግራይ ወጣቶችን እያገተና ወላጆችን እያሰረ ትውልድን ለማጥፋት እየሠራ ነው ያሉት ቡድኑ፤ የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ወደ ጎን በመተው ለታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጥቅም እየሠራ እንደሚገኝና ሕዝቡም በፈቃደኝነት ከእሱ ጋር እንደማይዋጋ በተግባር እያረጋገጠ መሆኑን አጋልጠዋል።
አቶ ጉዕሽ የፌዴራል መንግሥት እስካሁን ላሳየው የሰላም ትዕግሥትና ጥረት ምስጋና አቅርበው፣ አሁን ላይ ግን የቡድኑ እንቅስቃሴ ወደ አደገኛ ደረጃ በመሸጋገሩ የትግራይን ሕዝብ ለማዳንና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ሕገ-መንግሥታዊና ፖለቲካዊ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለበት በማሳሰብ፣ መላው የትግራይ ሕዝብ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጎን ቆሞ ይህንን ኋላቀር ቡድን እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1