ሰውየው ስንት ናቸው ?

- Advertisement -
Sidebar AD

በኤፍሬም የማነ

#Ethiopia | የፊፋው አድራጊ ፈጣሪ ፈላጭ ቆራጭ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ለአጅሬ ትራምፕ ታዘው እስካደሩ ድረስ በሰሜን አሜሪካ ሰማይ ስዞር ውዬ ባድር ማን ይነካኛል ማንስ ይከለክለኛል ምንስ አገባችሁ የሚሉ ይመሥላሉ ? የሰውየው የግል ጄት በአሜሪካ ካናዳ ሜክሲኮ ሰማይ በሚሊዮን ዶላሮች ወጪ እየተንፈላሰሰች ነው ። ምክንያታቸው ደግሞ ሁሉንም የኳስ ጨዋታ በንቃት የእግር ኳሱ ዋና አለቃ እያየሁ ነው ለማለት !!!

ለፕላኔታችን የአየር ንብረት ጥበቃ የበኩላቸውን እንደሚወጡ በተደጋጋሚ ሰውየው ቢናገሩም፣ በዓለም ዋንጫው ወቅት በግል ጄት (Private jet) ወደ 35,000 ማይልስ የሚጠጋ ርቀት በቀናቶች ውስጥ ተጉዘዋል።

ሰውየው ከስቴዲየም ስቴዲየም ከጨዋታ ጨዋታ ከከተሞች ከተሞች እየዘለሉ በርካቶችን አስገርመዋል ። እንዴት በዚህ ፍጥነት ከጨዋታ ጨዋታ መታየታቸው ዕኚህ ሰው ስንት ናቸው ያስባለም ሆኗል። ​የፊፋው ፕሬዝዳንት በ18 ቀናት ውስጥ ብቻ 27 ጨዋታዎች ላይ ታይተዋል።

ነገሩ ጨዋታዎችን ለመከታተል ነው ወይስ ለፎቶ የሚለው ጥያቄ ይቆይና ዓለም ዋንጫው በሚካሄድባቸው 16 ከተሞች በየጨዋታው አንዴ በሸሚዝ አንዴ በሱፍ ከበርካታ ዝነኞች መታየታቸው የፊፋው አለቃ የኳስ ፍቅር ሱስ ነው ወይስ የሰሜን አሜሪካ ፈጣን የአየር ላይ ጉብኝት ያስብላል ።

ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በምድብ ጨዋታዎች ወቅት ወደ ተለያዩ አስተናጋጅ ከተሞች 27 ያህል በረራዎችን ያካሄዱ ሲሆን እስከ ዓለም ዋንጫው ፍፃሜ ድረስ ይህ ቁጥር በዕጥፍ ሊጨምር እንደሚችል እየተዘገበ ነው ።

የዓለም ዋንጫው በሚካሄድባቸው አሜሪካ ካናዳ እና ሜክሲኮ 16 ከተሞች የአውሮፕላን በረራ የማይል ርቀቶች አጭሩ እስከ 92 Mile 148 km ሲሆን ረጅሙ ደግሞ 2800 mile 4507 km ይደርሳል ።

አንዳንዶቹ በረራዎች ሁለት ሶስት አራት ሰዓታት ይፈጃሉ ። እናም በጥቅሉ እስካሁን በ18 ቀናት ውስጥ በ26 ጨዋታዎች ላይ ከምድብ አስከ ጥሎ ማለፍ የዛሬ ጨዋታዎች ድረስ ሰውየው አንዱ ጨዋታ እንዳለቀ ወደ አንዱ ከተማ ከስቴዲየም ስቴዲየም ከከተማ ከተማ ከሀገር ሀገር በvvip ኢንትራንስ ሲዟዟሩ መታየታቸው የፊፋን በረብጣ ቢሊዮን ዶላሮች የደለበ የካዝና ቋት እንደ ልባቸው ማድረጋቸው ይቆይና ሰውየው ለመሆኑ ስንት ናቸው በርካቶችን ያስባለ አነጋጋሪ የዓለም ዋንጫው ጉዳይ ሆኗል ።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: