ለነፃ የልብ ሕክምና ተዘጋጁ!

- Advertisement -
Sidebar AD

* ከ54 በላይ የልብ ሕክምና ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው

#Ethiopia | «ኸርት አታክ ኢትዮጵያ» የበጎ አድራጎት ድርጅት ከ54 በላይ የልብ ሕክምና በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎችን ያቀፈ የሕክምና ቡድን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከ200 በላይ ነፃ የልብ ሕክምናና የቀዶ ሕክምና አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ድርጅቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የሕክምና ቡድኑ ከህንድ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ሩዋንዳ እና ቦትስዋና የተውጣጡ የልብ ስፔሻሊስት ሐኪሞች፣ ነርሶችና ሌሎች የጤና ባለሙያዎችን ያካተተ መሆኑን ገልጿል።

የድርጅቱ መስራች ዶ/ር ኦብሴ መርዕድ እንዳሉት፣ በዚህ አምስተኛ የሕክምና ዘመቻ ከ200 በላይ የልብ ቀዶ ሕክምናዎችና ሌሎች የካርዲዮሎጂ ፕሮሲጀሮች ይከናወናሉ።

አገልግሎቱም በኮሪያ ሆስፒታል፣ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል እና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ይሰጣል።

«ኸርት አታክ ኢትዮጵያ» ከዚህ ቀደም ባከናወናቸው አራት የነፃ የሕክምና ዘመቻዎች ወደ 480 የሚጠጉ የልብ ቀዶ ሕክምናዎችን በነፃ ማከናወኑን ገልጾ፣ በቀጣይም ተመሳሳይ ድጋፎችን እንደሚያስቀጥል አስታውቋል።

ድርጅቱ በመጨረሻም ነፃ የልብ ሕክምና ለማግኘት የሚፈልጉ ዜጎች ለቀጣይ እሁድ እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

ሆኖም የሕክምና አገልግሎቱ በአብዛኛው በተዘጋጁ የልብ ሕክምና ማዕከላት ቀድሞ ክትትል ላይ ከነበሩ እና በስፔሻሊስት ሐኪሞች ከተለዩ ታካሚዎች መካከል እንደሚሰጥም ገልጿል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#ኸርትአታክኢትዮጵያ
#የልብህክምናበኢትዮጵያ
#ጥቁርአንበሳሆስፒታል
#ጌጡተመስገንሚዲያናኮሙኒኬሽንስ
#Getutemesgenmediacommunications






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: