የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዘንድሮው በጀት ዓመት 80 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ
ባንኩ በበጀት ዓመቱ 80 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ በማግኘት ስኬታማ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጿል።
የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለጹት፣ ይህ ትርፍ ባንኩ ባለፉት ጊዜያት ያጋጥሙት ከነበሩት ችግሮች በመውጣት ያስመዘገበው ትልቅ ስኬት ነው።
ፕሬዝዳንቱ የባንኩን የሥራ አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ ባንኩ ከስድስት ዓመታት በፊት ከነበረበት ችግር ወጥቶ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ደረጃ ቀዳሚ ከሚባሉ ጠንካራ ባንኮች ተርታ መሰለፉን ተናግረዋል።
ባንኩ ለደረሰበት ከፍተኛ የትርፍ መጠን በዋናነት ለግል ዘርፉ የሰጠው ትኩረት፣ የተበላሸ ብድር መጠን መቀነሱ እና የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት መስፋፋት በምክንያትነት ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ባንኩ በበጀት ዓመቱ 648 ቢሊዮን ብር አዲስ ብድር እንደሰጠ የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፣ ከዚህ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነው ለግል ዘርፍ የቀረበ መሆኑን አስረድተዋል።
ይህም ከስድስት ዓመታት በፊት 90 በመቶው ብድር ለመንግሥት ተቋማት ይሰጥ ከነበረበት አሠራር የተቀየረ የሪፎርም ውጤት መሆኑን በመጥቀስ፤ በበጀት ዓመቱ ግን 90 በመቶ የሚሆነውን ወይም 588 ቢሊዮን ብሩን ለግል ዘርፍ ማበደሩን ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ ከ707 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ፣ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘቡን ከ2 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ብር በላይ ማድረሱን ገልጸዋል።
ባንኩ በቀጣዩ ዓመት 832 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ለማሰባሰብ፣ እንዲሁም ገቢውን 360 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ማቀዱን በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
በአጠቃላይ ባንኩ የአሠራር ሥርዓቱን በማሻሻልና ሪፎርም በማድረግ፣ በሀገሪቱ ከሚገኙ ባንኮች ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ እንደሚገኝ ተገልጿል።

No comments yet.