#FastMereja I በፊሊፒንስ ማኒላ በተካሄደውና ከ170 በላይ ሀገራት በተሳተፉበት የዓለም አቀፍ ትሬዲሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን (GTTF) ዓለም አቀፍ ጉባኤና ሻምፒዮና ላይ የኢትዮጵያ ተወካይና የEGTTF ተጠሪ ማስተር ኤዶንያስ ጌቱ ከአፍሪካ በመገኘት የሀገሪቱን ባንዲራ በክብር አስጠብቀዋል። ማስተሩ በውድድሩ ላይ ላሳዩት ከፍተኛ ሙያዊ ብቃትና መሪነት የላቀው “Outstanding LEADER AWARD” የተሰኘ የክብር ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን፣ ማርሻል አርትስን ከሀገራዊ የቱሪዝም ዘርፍ ጋር በማስተሳሰር “ስፖርታዊ ቱሪዝምን” ለማሳደግ ያለመ አዲስ ስትራቴጂካዊ ብሄራዊ ራዕይም ይፋ አድርገዋል።
ለሰባት ቀናት በደመቀ ሁኔታ በተካሄደው በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ማስተር ኤዶንያስ ጌቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዳኝነት (Umpire) ከፍተኛ ሙያዊ ብቃታቸውን አሳይተዋል። ከዚህም በተጨማሪ እጅግ ማራኪና አስደናቂ የነበረውን የዲሞንስትሬሽን ቡድን (Demonstration Team) በበላይነት በመምራት መድረኩን ያስደመሙ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎም ስፖርቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስፋፋትና በመሪነት ላሳዩት ወደር የለሽ አስተዋጽኦ በታላላቅ ግራንድ ማስተሮች ፊት የላቀ መሪነት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ይህ ታላቅ መድረክ የውድድር ስፍራ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ አዲስ የኢኮኖሚና የባህል በር የከፈተ ሆኗል። በማስተር ኤዶንያስ መሪነት ይፋ የሆነው አዲሱ ራዕይ የስፖርቱን እሴቶች ከቱሪስት መዳረሻዎች ጋር በማጣመር የውጭ ሀገር ስፖርተኞችንና ጎብኚዎችን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ ያለመ ነው።
በፕሮግራሙ ላይ የታደሙት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አንጋፋ የቴኳንዶ ባለሙያዎች፣ ማስተሮች እና ግራንድ ማስተሮች ይህንን ራዕይ በከፍተኛ ደረጃ ያደነቁ ሲሆን፣ ማርሻል አርትስ የሀገርን ባህልና ገጽታ ለማስተዋወቅ ያለውን ታላቅ አቅም በተግባር ለማዋል ሙሉ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል።



Source: FastMereja








No comments yet.