በአርባ ምንጭ ከተማ የ12 ዓመቷን የገዛ ሚስቱ እህትን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
ተከሳሽ አቶ ኃይማኖት ዮሐንስ የተባለው ግለሰብ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊት ሰዓቱ በውል በማይታወቅበት በአርባ ምንጭ ከተማ ሼቻ ክፍለ ከተማ ዶይሳ ቀበሌ ልዩ ስፍራው አሻም ሆቴል ጀርባ አከባቢ የባለቤቱ እህት በሆነች ታዳጊ ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል መፈፀሙ ተገልጿል።
ተከሳሽ ከእሱ እና ከባለቤቱ ጋር በአንድ ቤት በሥራ አጋዥነት የምትኖረውን ዕድሜዋ 12 ዓመት የሆነችውን የግል ተበዳይን ባለቤቱ ለስራ በሄደችበት ምሽት አጋጣሚውን በመጠቀም የፖርኖግራፊ (ልቅ የወሲብ) ፊልም በቴለቪዥን በመክፈት እንድትመለከት ካደረገ በኋላ የግል ተበዳይ የለበሰችውን ልብስ አውልቆ በመራቢያ አካሏ እና በመቀመጫዋ በተደጋጋሚ ጊዜ የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈፀመባት እና ድርጊቱን ለሰዎች እንዳትናገር ያስጠነቀቃት ቢሆንም በድርጊቱ ምክንያት በግል ተበዳይ ላይ በተከሰተ ህመም ተበዳይ ጉዳዩን ለጎረቤት በመንገሯ የወንጀል ምርመራ ሂደቱ ተጀምሮ ለውጤት በቅቷል ሲል የዓቃቤ ክስ መዝገብ ያስረዳል።
የወንጀል ድርጊቱ መፈፀም ሪፖርት የደረሰው የከተማው ፖሊስ መምሪያ የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ልዩ መርማሪ ከዐ/ሕግ ጋር በመቀናጀት የምርመራ መዝገቡን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ ክስ ይመሰርታል።ጉዳዩን የተመለከተው የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ብይን ሰጥቷል ።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.