የንግድና የቴክኖሎጂ ትስስርን የሚያጠናክረው “የጣሊያን ዘመናዊ አኗኗር 2026” (Italian Smart Living) በአዲስ

- Advertisement -
Sidebar AD

🇪🇹🤝🇮🇹 የንግድና የቴክኖሎጂ ትስስርን የሚያጠናክረው “የጣሊያን ዘመናዊ አኗኗር 2026” (Italian Smart Living) በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የዲዛይን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመው ከፍተኛ የቢዝነስ እና የዲዛይን ኹነት በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም ሊካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል።

📅 የሁነቱ መርሃ-ግብር
ቀን፦ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ከጁላይ 7 እስከ 9 ቀን 2026
*ቦታ፦በአዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም

✨ በሁነቱ ላይ ምን ምን ይጠበቃል?

🛍️ ልዩ ኤግዚቢሽን እና የB2B ትስስር

ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የጣሊያን የቤት ዕቃዎች (Furniture)፣ የሥነ-ሕንጻ ብርሃን ቴክኖሎጂዎች፣ ሴራሚክስ እና እብነበረድ የሚቀርቡበት ሲሆን፤ የሁለቱን ሀገራት ኩባንያዎች በቀጥታ የሚያገናኝ የንግድ ትስስር መድረክ ተዘጋጅቷል።

🏗️ ሙያዊ ሴሚናሮች፦

በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባለው ‘Interni Magazine’ አወያይነት በዘላቂ የከተማ ልማት፣ በሃይል ቆጣቢ ህንፃዎች እና በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ የሀገር ውስጥ፣ የጣሊያንና የቀጣናው (ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ) ምሁራንና ጋዜጠኞች የሚሳተፉበት ውይይት ይደረጋል።

🎓 የዲዛይን ማስተር ክላስ እና ልዩ ውድድር፦

በታዋቂው አርክቴክት ዱቺዮ ግራሲ (Arch. Duccio Grassi) የሚመራ ልዩ የስልጠና መርሃ-ግብር የሚሰጥ ሲሆን፤ በታሪካዊው የመርካቶ የንግድ ቀጠና ላይ ያተኮረ የመርካቶ ከተማ መልሶ ማልማት ውድድር (Merkato Urban Regeneration Competition) በይፋ ይጀመራል።

🏛️ የMade in Italy” ታሪክ ትዕይንት

በአለም አቀፍ የ“Made in Italy” ቀን ምክንያት በማድረግ በጣሊያን የምርት መለያዎች ሙዚየም አማካኝነት ታዋቂ ብራንዶች ያለፉበትን የዲዛይን እድገት የሚያሳይ ልዩ ኤግዚቢሽን ለዕይታ ይቀርባል።

📌 ለተደራሲያን የቀረበ ማሳሰቢያ
ሁነቱ ለመጀመሪያዎቹ ቀናት ለባለሙያዎችና ለቢዝነስ ተቋማት (B2B) ብቻ ክፍት የሚሆን ሲሆን፤ በመጨረሻው ቀን ማለትም በሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ጁላይ 9) ለማንኛውም ፍላጎት ላለው የህዝብ ክፍል እና ለዲዛይን አፍቃሪዎች ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆኖ ክፍት ይደረጋል።

#ItalianSmart Living2026 #AddisAbaba #Ethiopia #Italy #Business #Design #Architecture #Innovation


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2