እነሆ የልብ ጤናችሁን ለመጠበቅ ቁልፍ የሆኑ ምክሮችየልብና የደም ሥር በሽታዎች በዓለም የሞት ዋና ምክንያቶች መካከል ቢሆኑም፣ …

- Advertisement -
Sidebar AD
እነሆ የልብ ጤናችሁን ለመጠበቅ ቁልፍ የሆኑ ምክሮች

የልብና የደም ሥር በሽታዎች በዓለም የሞት ዋና ምክንያቶች መካከል ቢሆኑም፣ በአንድነት ይህን መቀየር እንችላለን!
🔹 እንቅስቃሴ ያድርጉ፡ በሳምንት ቢያንስ ለ150 ደቂቃ መካከለኛ የሆነ እንቅስቃሴ ያድርጉ። መራመድ፣ ብስክሌት መንዳት ወይም በመደነስ መዝናናት የሚረዱ ናቸው።
🔹 ጤናማ ምግብ ይመገቡ፡ ብዙ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ እህል እና ቀላል ፕሮቲኖችን በምግቦቻቹ ጨምሩ። ስብ፣ ስኳርና ጨውን ያስወግዱ።
🔹 ጭንቀትን ያስቀንሱ፡  ሜዲቴሽን፣ ዮጋ፣ ወይም ጥልቅ እስትንፋስ በመውሰድ ጭንቀትን ቀንሱ እና ልብን ጤናማ ያድርጉ።
🔹 ማጨስ ማቆም፡ ትምባሆን ማጨስ ማቆም በልብ በሽታ የመያዝ እድልን እጅግ ይቀንሳል።
🔹 መደበኛ ምርመራ ያድርጉ፡ የደም ግፊት፣ ኮሌስትሮል መጠን እና አጠቃላይ የልብ ጤና በመደበኛ ምርመራ በማድረግ ጤናዎን ይከታተሉ።
🔹 በቂ ውሃ ይጠጡ፡  በስኳር የተሞሉ መጠጦችን ያስወግዱ። ይህ የሰውነት ተመጣጣኝ ክብደትን ለመጠበቅ ይረዳል።
እነዚህን ልምዶች በመከተል እና በጤና ጉዞአችን እርስ በርስ በመደጋገፍ እንትጋ።
አስታውሱ፤ ለጤናማ ነገ ዛሬ ልብዎን ይንከባከቡ !
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1