ኢሰመኮ በትግራይ ክልል የወጣው “የግዳጅ ወታደራዊ አዋጅ” በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ክልል ወጣቶችን በግዳጅ ወደ ውትድርና የማሰማራት እና ሐሳብን የመግለጽ መብትን የመገደብ ተግባራት ከሕገ መንግሥቱና ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር ስለሚጣረሱ በአፋጣኝ ሊቆሙ እንደሚገባ አሳሰበ።
ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል የክልሉ ጊዜያዊ ምክር ቤት “የትግራይ ሕዝብን ሕልውና ለመጠበቅ” በሚል ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የግዳጅ ውትድርና ሰነድ አውጥቶ ሥራ ላይ ማዋሉን አረጋግጧል።
ለግዳጅ ውትድርና ጥሪውን የማይቀበል ሰው እስከ 50 ሺህ ብር ቅጣት፣ የክልሉን ውሳኔ የሚተቹና የሚቃወሙ ደግሞ እስከ 25 ዓመት ጽኑ እስራትና የንብረት መወረስ ይፈረድባቸዋል።
ይሄን ተከትሎም የጸጥታ አካላት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ሰዎችን የመያዝ እና የመፈተሽ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል ማለቱን ሐራምቤ ሬድዮ ከመግለጫው ተመልክቷል።
በአብያተ ክርስትያናት፣ በገበያና በቤት ለቤት አሰሳ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት፣ ተፈናቃዮችና የአእምሮ ሕሙማን በግዳጅ እየታፈሱ መሆኑ ተረጋግጧል። ይህም እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠር የሚችል የጉልበት ብዝበዛ ነው።
በክልሉ አዋሳኝ አካባቢዎች (ራያና አፋርን ጨምሮ) በታጠቁ ኃይሎች መካከል በተነሱ ግጭቶች የሰው ሕይወት የጠፋ ሲሆን፣ በርካታ ዜጎች ያለ ምግብና መጠለያ ተፈናቅለዋል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ይህ ተግባር የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት የሚጥስና አንጻራዊ ሰላሙን ወደ ኋላ የሚመልስ በመሆኑ፣ የግዳጅ ውትድርና ሰነዱ ተፈጻሚነት በአስቸኳይ እንዲቆም እና የፖለቲካ ልዩነቶች በሰላማዊ ውይይት ብቻ እንዲፈቱ በጥብቅ አሳስበዋል።
@Seledadotio

No comments yet.