አዲስ መጽሐፍ | የአእምሯዊ ንብረት ሕግ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የሕግ ባለሙያና ደራሲ ዳዊት መ. በዛብህ (Dawit M. Bezabih) የጻፉት “የአእምሯዊ ንብረት ሕግ (Intellectual Property Law)” መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።

ዳዊት በሕግ ዘርፍ በአማርኛ ቋንቋ እምብዛም ያልተዳሰሱ ወሳኝ ርዕሰ ጉዳዮችን በማቅረብ የሚታወቅ ጸሐፊ ሲሆን፣ በዚህ መጽሐፉም የአእምሯዊ ንብረት ሕግን ከመሠረቱ ጀምሮ በጥልቀት ያብራራል።

በመጽሐፉ ውስጥ፦

✔️ የአእምሯዊ ንብረት ሕግ ምንነት፣ ታሪክና ዓላማ
✔️ የፈጠራ ባለቤትነት (Patent) እና የምዝገባ ሂደት
✔️ የቅጂ (Copyright) እና ተዛማጅ መብቶች
✔️ የንግድ ምልክት (Trademark)
✔️ የንግድ ሚስጥር (Trade Secret)
✔️ የአእምሯዊ ንብረት ሕግ ከሰው ሠራሽ አስተዋይነት (AI) እና ከዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጋር ያለው ግንኙነት
በግልጽና በቀላል አቀራረብ ተዳስሰዋል።

⚖️ ለሕግ ተማሪዎች፣ ጠበቆች፣ ደራሲያን፣ ፈጠራ ባለቤቶች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና በዘርፉ ፍላጎት ላላቸው ሁሉ ጠቃሚ የማጣቀሻ መጽሐፍ ነው።

አንብቡት!
በJafer Books ያገኙታል።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: