በድሬዳዋ በክረምት ወቅት በተለያየ ጊዜ ጎርፍ እንደሚከሰት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ፍቅሬ እንደገለፁት ይህ ሁኔታ ዳግም አደጋ እንዳያስከትል ስድስት ቦታዎችን ቀድሞ በመለየት የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት በበጋ ወቅት ጀምሮ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተብለው የተለዩ ከ 170 በላይ ሰዎች ለጊዜያዊነት ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ መደረጉን ገልፀዋል።
ጎርፍ የሚበዛባቸው አካባቢዎች አስቀድሞ እርከን እየተሰራላቸው እንደሆነና በከተማዋ ከጥገና ባለፈ ማህበረሰቡ በቂ የሆነ ግንዛቤ እንዲያገኝ እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።
ከዚህ በፊት በከተማዋ የጎርፍ አደጋ ሲከሰት ብዙ ንብረትን ጨምሮ በሰዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እንደሚያስከትል የገለፁት አቶ ቴዎድሮስ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ይህ ችግር እየተቀረፈ መምጣቱን ገልጸዋል።
አሐዱ_

Source: Yeneta Tube









No comments yet.