🎭
በዉቢቱ ባህርዳርና በነገሥታት መዲና ጎንደር ከተማ የተመልካቾችን ልብ በመግዛት ከፍተኛ አድናቆትና ውዳሴ ያተረፈው “እንዛታ” ትውፊታዊ ቲያትር ወደ አዲስ አበባ አቅንቷል ።
ይህ የመድረክ ድንቅ ሥራ በአዝማሪዎች ሕይወት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ዜማን ከፍልስፍና፣ ቃልን ከታሪክ፣ ባህልን ከዘመናዊ የመድረክ ጥበብ ጋር በልዩ ክህሎት ያጣመረ ትዉፊታዊ ቲያትር ነው።
📍 የእይታ መርሃ ግብር
🎭 ዛሬ እሁድ ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም.
ብሔራዊ ቲያትር — ከቀኑ 8፡00
🎭 ማክሰኞ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም.
ብሔራዊ ቲያትር — 11፡00
🎭 ሀሙስ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም.
ሀገር ፍቅር ቲያትር — ከቀኑ 10፡30 ይታያል ።
ከቤተሰብዎ፣ ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር በመታደም፣ የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክእና የመድረክ ጥበብ በአንድ የሚያገናኘውን ይህን ድንቅ ሥራ እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል ።



Source: GetuTemesgen









No comments yet.