“ደብረጽዮን ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር በሚስጢር ተገናኝተዋል!” -ጌታቸው ረዳየጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አማካሪና የቀድሞው የትግራ…

- Advertisement -
Sidebar AD
“ደብረጽዮን ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ
ጋር በሚስጢር ተገናኝተዋል!”
-ጌታቸው ረዳ
የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አማካሪና የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በሚስጢር መገናኘታቸውን በመግለጽ ከባድ ክስ ሰንዝረዋል። ጌታቸው ረዳ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ ደብረጽዮን ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር የተገናኙት የጦር መሣሪያ ድጋፍ ለመጠየቅ እንደነበር ገልጸዋል።
እንደ ጌታቸው ገለጻ፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለሕወሓት ሊቀመንበር በሰጡት ምላሽ በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ላይ ድጋሚ ጦርነት ከከፈታችሁ በኋላ አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርግላችኋለን ማለታቸውን ተናግረዋል። ሆኖም ግን ይህ ምስጢራዊ ስብሰባ መቼ እና የት ቦታ እንደተካሄደ ጌታቸው ረዳ በጽሑፋቸው ላይ የጠቀሱት ነገር የለም።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2