#Ethiopia | የትራፊክ አደጋ ካደረሱ አሽከርካሪዎች ውጭ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የማገድ ውሳኔ የደንብ ቁጥር 557/2016 ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ እስከሚጸድቅ ድረስ ለጊዜው እንዲቆም መደረጉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ የዲጂታል የትራፊክ ቁጥጥርና ቅጣት ማስፈጸሚያ ስርዓትን በመዘርጋት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016 መሠረት የቅጣት አወሳሰንን እየተገበረ ይገኛል።
ደንቡ በተደጋጋሚ ጥፋት ፈጽመው የነጥብ ጣሪያ ላይ የደረሱ አሽከርካሪዎች ፈቃዳቸው ታግዶ የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ፣ ወይም አስቀድመው ስልጠና ወስደው ነጥብ የሚያስቀንሱ ደንብ ተላላፊዎች የእውቅናና ክህሎት ስልጠና ማረጋገጫ ሲያቀርቡ እግዱ እንደሚነሳ ያዝዛል።
ነገር ግን ደንቡ በሌሎች ክልሎች ሳይተገበር በአዲስ አበባ ብቻ በመተግበሩ በአሽከርካሪዎች ዘንድ የፍትሃዊነት ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል። ባለስልጣኑ ይህንን አሰራር ለመንገድ ደህንነት ፈንድ አገልግሎት ማሳወቁን ተከትሎ ተቋሙ ባስLocation ደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል።
በምላሹም የተሃድሶ ስልጠና አሰጣጥን ግልጽ የሚያደርግ ዝርዝር መመሪያ ተዘጋጅቶ ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩንና በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ አሰራር ለመዘርጋት ሲባል የፈቃድ እግዱ ለጊዜው እንዲዘገይ መወሰኑን ገልጿል።
በዚሁ መሠረት የገንዘብ ቅጣቶቹ እንደተጠበቁ ሆነው፣ መመሪያው ጸድቆ እስከሚወጣ ድረስ ከትራፊክ አደጋ ጋር የተያያዙ ጥፋቶች ውጭ በነጥብም ሆነ ክፍያ በመዘገየታቸው ምክንያት ቀደሙ የታገዱና በቀጣይ የሚታገዱ አሽከርካሪዎች እግድ ለጊዜው ይነሳል።
ሆኖም አሽከርካሪዎች ያሉባቸውን የገንዘብ ቅጣት የመክፈል ግዴታ እንዳለባቸው ባለስልጣኑ አሳስቧል።
#addisababa #trafficmanagement #driverlicense #ethiopiannews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.