ፕሬዝዳንቷ ከየትኛውም የአሜሪካ ተቋም ጋር ግኑኝነት እንዳያደርጉ ታገዱ

- Advertisement -
Sidebar AD

*አሜሪካ በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ላይ ማዕቀብ ጣለች

#Ethiopia | የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ጃፓናዊቷ ዳኛ ቶሞኮ አካኔ ላይ ማዕቀብ ጥሏል።

ማዕቀቡ በአሜሪካ የሚገኝ ማንኛውም ሀብታቸው እንዲታገድ እና ከአሜሪካ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲሁም ከማንኛውም የአሜሪካ ዜጋ/ተቋም ጋር የንግድና የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ የሚያደርግ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ እንደገለጹት ፍርድ ቤቱ የአሜሪካ እና እስራኤል ባለስልጣናት ለመክሰስ እና ለማሰር የሚደረገውን ጥረት በመምራታቸው ምክንያት የተጣለ እርምጃ ነው ብለዋል።

ፍርድ ቤቱ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና በቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ላይ በጋዛ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የእስር ማዘዣ ማውጣቱን ተከትሎ ውጥረቱ እየተባባሰ መጥቷል።

አሜሪካ የፍርድ ቤቱ አባል አይደለችም።

ነገር ግን የትራምፕ አስተዳደር ፍርድ ቤቱ የሀገራትን ሉአላዊነት እና የአሜሪካን እንዲሁም የእስራኤልን ጥቅም የሚጋፋ ነው በማለት ይከሱታል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#USA #international #court
#President #Japan
#sanction #Criminal


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2