አዋሽ ባንክ ዲጂታል የነዳጅ ክፍያ አግልግሎት መተግበሪያ አስጀመረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I ለደንበኞቹ የሚሰጠውን የባንክ አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ እየሰራ የሚገኘው አዋሽ ባንክ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እንዲሁም ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ዲጂታል የነዳጅ ክፍያ ስርዓት ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ለገሀር በሚገኘው ራስ ሼል ማደያ በይፋ አስጀምሯል። ይህ የአዋሽ ብር ፕሮ ዲጂታል የነዳጅ ክፍያ ለመፈጸም የሚያስችል ምቹ እና ቀላል መተግበሪያ መሆኑ ተገልጿል።

የክፍያ መተግበሪያው አጠቃቀም የባንኩ ደንበኞች የትም ሥፍራ ሆነው የነዳጅ ፍጆታ ክፍያዎቻቸውን በአዋሽ ብር-ፕሮ (AwashBirr-pro) የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በመጠቀም በኪው-አር ኮድ (QR code) እንዲሁም የደንበኛውን ስልክ በመጠቀም በUSSD የደንበኛውን የይለፍ ቃል በማስገባት ብቻ ክፍያ መፈጸም የሚያስችል ነው።

የመተግበሪያውን አጠቃቀም በተመለከተ ዝርዝር መመሪያ የተዘጋጀ ሲሆን በተዘጋጀው የአጠቃቀም መመሪያ መሰረትም በአዋሽ ብር-ፕሮ (AwashBirr-pro) የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በመጠቀም በጊዜ እና በቦታ ሳይገደቡ ሳምንቱን ሙሉ በፈለጉት ሰዓት ደንበኞቻችን የነዳጅ ክፍያቸውን መክፈል እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ የክፍያ ስርዓት መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ ባንኩ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ከበርካታ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በጋራ በመሥራት ላይእንደሚገኝም ተገልጿል።

ባንኩ የደንበኞቹን እርካታ በተፈለገው ደረጃ ለማሳደግ የዲጂታል አገልግሎቶቹን ተደራሽ፣ ምቹ እና ቀልጣፋ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን በመግለጽ ደንበኞቹ እና መላው ህብረተሰብ በአገልግሎቱ እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1