ኢትዮጵያ 6 የጭነት መርከቦችን ልትገዛ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ኢትዮጵያ ስድስት አዳዲስ የጭነት መርከቦች ልትገዛ መሆኑን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አስታውቋል።

ድርጅቱ ከስድስቱ መርከቦች ሁለቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገዝተው ወደ አገልግሎት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጿል።

ሁለቱ አልትራማክስ የደረቅ ብትን ጭነት መርከቦች እንደሆኑና 62 ሺህ ቶን የመጫን አቅም እንዳላቸው ተገልጿል።

ሌላኛው ኢቲዩ ኮንቴነር ጫኝ መርከብ ደግሞ ከ3 ሺህ እስከ 4 ሺህ ኮንቴይነር የመጫን አቅም እንዳለው ተመላክቷል።

መርከቦቹ የሀገሪቱን የገቢ ወጪ ንግድ ከማሳደግ አኳያ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸውም ተጠቁሟል።

የቀሪ አራት መርከቦች ግዥ በቀጣዮቹ ዓመታት እንደሚፈጸምም ነው የተገለጸው።

አሁን ላይ ኢትዮጵያ 10 መርከቦች ያሏት ሲሆን፣ 1ኛውና ዓባይ ፪ የተሰኘው መርከብ 63 ሺህ ቶን እንዲሁም ቀሪዎቹ ደግሞ ከ26 ሺህ እስከ 27 ሺህ ቶን የመጫን አቅም እንዳላቸውም ተጠቁሟል ሲል የዘገበው ኤፍ ኤም ሲ ነው።

የደራው መጽሔት፤ ፀሐይ አትጠልቅም!

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1