ሳዑዲ አረቢያ ከመጪው ጥር 1፣ 2026 ጀምሮ የቤት ሰራተኞች ክፍያ መንግስት በዘረጋው ስርዓት እንዲከፈል ወስናለች።በሳዑዲ አረ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ሳዑዲ አረቢያ ከመጪው ጥር 1፣ 2026 ጀምሮ የቤት ሰራተኞች ክፍያ መንግስት በዘረጋው ስርዓት እንዲከፈል ወስናለች።
በሳዑዲ አረቢያ የሚሰሩ የቤት ሰራተኞች ከመጪው ጥር 1፣ 2026 ጀምሮ ክፍያቸውን በተዘረጋው የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት እንደሚከፈላቸው ይህም የደመወዝ ጥበቃ እንደሚሰጣቸው እና ግልፀኝነትን እና ጊዜውን የጠበቀ ክፍያ እንዲሰጣቸው እንደሚያደርግ የሃገሪቱ የሰው ሃብት ሚኒስትር አስታውቋል።
ሰራተኞቹ ወቅቱን ጠብቆ ደሞዛቸው በጥሬ ገንዘብ ሳይሆን “ሙሳነድ” በተባለው ሥርዓት የሚከፈላቸው ሲሆን ያገኙትን ገንዘብም በተፈቀዱ መንገዶች ውጪ ላሉ ቤተሰቦቻቸው ማስተላለፍ ይችላሉ።
ሳዑዲ ይህንን ስርዓት ከ2024 ጀምሮ ወደ ስራ ለገቡ አዳዲስ ሰራተኞች መጠቀም የጀመረች ሲሆን የተለያዩ ሂደቶችን ካለፈ በኋላ ከ2026 ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ ይገባል ተብሏል።
በአዲሱ ሥርዓትም ሰራተኞቹ የሂጂራ ወር መጨረሻ ላይ በኮንትራታቸው መሰረት ክፍያቸውን ያገኛሉ ተብሏል።
አዲሱ ሥርዓትም የቤት ሰራተኞች ጊዜውን የጠበቀ ክፍያ እንዲያገኙ በማስቻል ከሚጠብቃቸው መንገላታትና የክፍያ ማጣት ይጠብቃቸዋል።
ዘገባው የዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ ነው።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1