የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ የህይወት ታሪክ (በአጭሩ)

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | እዚህ አዲስ አበባ ኡራኤል አካባቢ በ1975 አመተ ምህረት ተወልዶ ያደገው ነጻነት ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ የህይወት ጥሪውን ለይቶ በማወቅ ለሚወደው የትያትር እና ጥበብ ራሱን የሰጠ እና በዚህም ለከፍተኛ ደረጃ የደረሰ አርቲስት ነበር፡፡

ተዋናይ፣ ኮሜዲያን፣ የቴሌቭዥን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ በኢትዮጵያ የፊልም እና የቴሌቭዥን ታሪክ ውስጥ የራሱን ልዩ የሆነ የአቀራረብ ስልት እና የትወና ጥበብ በማሳየት የሚታወቅ ባለሙያ ነበር።

ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖ የራሱን ትያትር በመድረስ እና ሴት ገጸ ባህሪን ወከሎ በመተውን ጭምር ተሰጣኦውን ያሳየው አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ይህን ችሎታውን በጠዋት የተረዱት የአማርኛ መምህሩ ቲቸር ተሻለ ካበረታቱት በኋላ በቲያትር ሙያ እንደገፋበት በተለያዩ መድረኮች ሲናገር አድምጠነዋል፡፡

በዩኒቨርስቲ የትያትር ክፍል ቆይታውም ከመምህራኑ ልዩ ድጋፍና አድናቆት የሚቸረው የያኔው ወጣት አርቲስት ነጻነት እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ሙያውን ለማሻሻል የሚጥር ድንቅ አርቲስት እንደሆነ የሙያ አጋሮቹ ይመሰከራሉ፡፡

* የኪነ-ጥበብ አጀማመር ሲናገር እንደሚሰማው ነፃነት ወደ ጥበቡ ዓለም የገባው ገና በወጣትነቱ ሲሆን፣ በተለይም በኮሜዲ ስራዎቹ የብዙዎችን ትኩረት መሳብ ችሏል። ከሰራቸው ስራዎች መካከል ፍሬሽ ማን፤ ያንቺው ሌባ፤ ኤፍቢአይ፤ ባለቀለም ህልሞች ይጠቀሳሉ””

* ነፃነት በተለይ የቴሌቭዥን ኢንዱስትሪን ከተቀላቀለ በኋላ ስራዎቹ በኢቢኤስ (EBS) ቴሌቭዥን ላይ “የቤተሰብ ጨዋታ” የተሰኘውን እጅግ ተወዳጅ ፕሮግራም ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን ሲያዘጋጅ እና ሲያቀርብ ቆይቷል። ይህ የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም በተለይ ከፍተኛ የህዝብ ተቀባይነት ያስገኘለት ሲሆን ከህጻን እስከ አዋቂ የፕሮግራሙ አድናቂ ብቻ ሳይሆን በግንባር እና በየቤቱ ተሳታፊ የሆነበት ነው፡፡

ነጻነት በጥያቄ እና መልሶች አጋጣሚ ድንገት የሚፈጥራቸው ቀልዶች በእጀጉ ሳቅን የሚያጭሩ ናቸው፡፡

ይህ ፕሮግራም በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዲኖረው የእርሱ ጨዋነት የተሞላበት አቀራረብ እና ቀልድ ትልቅ ድርሻ ነበረው።

ሌላው ቀርቶ በተለየ የንባብ አቀራረብ የሚሰራቸው ማስታወቂያዎች በሌሎች ያልታዩ ልዩ መታወቂዎቹ ነበሩ።

ነጻነት በስብዕና በስራ ባልደረቦቹ ዘንድ ተውዳጅ ሲሆን በትህትናው፣ ለስራ ባለው ትጋት እና ሁልጊዜም ሰውን ለማስደሰት ባለው ዝግጁነት የሚወደድ እንደሆነ መላው የኢቢኤስ የስራ ባልደረቦቹ ይመሰክሩለታል።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1