ደጃች ውቤ ሰፈር

- Advertisement -
Sidebar AD

“ከጋሽ ስብሃት” ጋር

በረ/ፕ ነቢዩ ባዬ

#Ethiopia | መምህራችን ጋሽ ተስፋዬ ገሰሰ (ነፍሱን ይማርልን) በአለም ሕይወቱ መጨረሻ አካባቢ “የመጨረሽታ መጀመርታ” የምትል መጽሃፍ አበርክቶልን ነበር።

በዓሉ ግርማ፣ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር እና እራሱን ጋሽ ተስፋዬን የመሳሰሉ ባለታሪኮች በመጽሃፏ ያነጋግሩናል። በትረካው ዐቢይ ስፍራ ካላቸው ስፍራዎች ቀዳሚዋ ናት። በጠቢባን መሰብሰቢያ ግሮሰሪዎቿ እና በምታስተናግድበት መንገድ። በአንዱ የመጽሃፏ ክፍል በደጃች ውቤ መኪና ውስጥ ተቀምጠው ስለበዓሉ ግርማ መሰወር ጋሽ ስብሃት እና ጋሽ ተስፋዬ ሲጫወቱ እናነባለን። ምስጢር መነጋገሪያቸው ናት ደጃች ውቤ። ሌላው መምህራችን ጋሽ አባተ መኩሪያም ስለደጃች ውቤ ብዙ ብዙ አጫውቶናል። እኛም በልጅነት ሰፈራችን ዘበኛ ሰፈር ቅርቧ-ትምህርት ቤታችን መነንም አጎራባቿ ስለነበሩ በደጇ ተመላልሰናል። ዩኒቨርሲቲ ሳለንም ከነጋሽ አባተ ጋር ተቀምጠን ብዙ ታሪክ ሰምተንባታል።
ግሮሰሪዎቹ በግሮሰሪ ኢትዮጵያዊያን ዐይን፣ እጅ እና ላብ ወደአስደማሚ ሕዝባዊ ሥፍራነት ሲለወጡ

ጋሽ ተስፋዬ የዘገባት ስፍራ፣
በዓሉ ግርማ የመጨረሻ ምሽቱን እንዳመሸባት የምትነገረን ስፍራ፣
ጋሽ አባተ ከጋሽ ስብሃት ጋር በብዙ የሕይወት ጉዳይ በመከሩባት ስፍራ፣
በዛሬዋ የልጆች የተስፋ መስክ አራዳ ፓርክ ደጃች ውቤ ላይ የስብሃት ገብረእግዚአብሔር ሀውልት በጎዳናዋ ዳር ተቀመጠ።
ለጤና ተስማሚ በሆነው ነፋሻማ መስክ የነጋሼን ዘመን በጎ በጎውን ጤና ጤናውን ትውልድ ያወሳ ዘንድ እነሆ የጠቢብ ሀውልት ቆመ።
ከጋሽ ፀጋዬ ሀውልት አጠገብ ተቀምጬ ለልጆቼ “ይኽውላችሁ ጠቢብ ሰው ትልቅ ነው፣ ሀውልት ይሰራለታል” እንዳልኩ ሁሉ አሁንም ለልጆቼ በሀገሬ ስለጠቢብ መከበር በኩራት የማስረዳበት ቋሚ ማስታወሻ አገኘሁ።

ምስጋና ለሰሩ ሁሉ።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: